አይቀርም (Ayqerem) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Tekeste Getnet 6.jpg


(6)

መጀመሪያ
(Mejemeriya)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፩ (2019)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:15
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

ሞላ አልሞላ የምለው ጉዳይ ቢኖረኝም
አለማመስገን እኔ ከቶ አይሆንልኝም
እኔ እንደ ልማዴ መዘመር ስጀምር
ባስጨነቀኝ ላይ ዛሬም ይገለጣል ክብር

ጉዳይ አለኝ የማዋይህ
ለልቤ ንጉስ ማንጎራጉርልህ
ነገር አለኝ የማዋይህ
ለልቤ ንጉስ ማንጎራጉርልህ

ምስጋና የሚሠዋ ማዳንህን እንዲያይ
በርግጥ ለሚወዱህ መላ አለህ ከሰማይ

ደግሞ እድሉ ደርሶኝ
ደግሞ ሳይገባኝ
ደግሞ በራሱ ፀጋ
ደግሞ ዘምር ካለኝ
ደግሞ እንዲህ እንድያ የሚል
ደግሞ ቆስቋሽ ለምኔ
ደግሞ የተሰራልኝ
ደግሞ በቂ ነው ለኔ

ያለው አይቀርም አምናለሁ
ዝማሬ ካፌ አይታጣ
የካሳ ጊዜ ይሆናል
ቀን ቆጥሮ ለኔ ሲመጣ
እግዚአብሔር ነው ጉልበቴ
መዝሙር በለሊት የሰጠኝ
ቃል ገብቶልኛል አውቃለሁ
ላይጥለኝ ደግሞ ላይተወኝ