ተመሥገን (Temesgen) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Tekeste Getnet 4.jpg


(4)

እወራረዳለሁ
(Eweraredalehu)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2004)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:00
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

መውጣቴ ፡ መግባቴ ፡ በአንተ ፡ ተጠብቆ
ከእኔ ፡ ጋር ፡ እንዳለህ ፡ ጠላቴ ፡ እንኳን ፡ አውቆ
ይሸሸኝ ፡ ገመረ ፡ በሄድኩበት ፡ ስፍራ
ሁሉን ፡ አስረገጥከኝ ፡ ሆነህ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
ለአንተ ፡ ሲያንህ ፡ ነው (፬x)

ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ ስምህን ፡ ልባርከው
ያንን ፡ ክፉ ፡ ዘመን ፡ ያለፍኩት ፡ በአንተ ፡ ነው
እልፍ ፡ ቃል ፡ ቢነገር ፡ አይገልጥህምና
መቅደስህ ፡ ገብቼ ፡ ልበል ፡ ጎንበስ ፡ ቀና (፪x)

አዝ፦ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን
አሳልፈኸኛል ፡ ያንን ፡ ክፉውን ፡ ቀን
ሌላ ፡ ቃል ፡ የለኝም ፡ ልበልህ ፡ ተመስገን
አሳልፈኸኛል ፡ ያንን ፡ ክፉውን ፡ ቀን
ሌላ ፡ ቃል ፡ የለኝም ፡ ልበልህ ፡ ተመስገን (፪x)

ምክንያት ፡ ፈልጌ ፡ ላመስግን ፡ እንጂ
ሰበብ ፡ ፈልጌ ፡ ልዘምር ፡ እንጂ
ስላልጠፋሁኝ ፡ ዛሬም ፡ ከአንተ ፡ ደጅ (፬x)

ምክንያት ፡ ፈልጌ ፡ ላመስግን ፡ እንጂ
ሰበብ ፡ ፈልጌ ፡ ልዘምር ፡ እንጂ
ስላልጠፋሁኝ ፡ ዛሬም ፡ ከአንተ ፡ ደጅ (፯x)