ሲከፋኝ (Sikefagn) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Tekeste Getnet 4.jpg


(4)

እወራረዳለሁ
(Eweraredalehu)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2004)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:48
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

አዝ፦ ከአንተ ፡ በላይ ፡ ለእኔ ፡ የለምና ፡ ለእኔ
አንስቼ ፡ አልጠግብህም ፡ ኢየሱስ ፡ መድህኔ
ከአንተ ፡ በላይ ፡ ለእኔ ፡ የለምና ፡ ለእኔ
አውርቼ ፡ አልጠግብህም ፡ ኢየሱስ ፡ መድህኔ

ዘመን ፡ ሲከፋ ፡ ቀን ፡ ሲለዋወጥ
አንተ ፡ ግን ፡ ያው ፡ ነህ ፡ የማትለወጥ
ሁሉን ፡ ለይቼ ፡ አይቼዋለሁ
እንዳንተ ፡ ሚሆን ፡ የት ፡ አገኛለሁ
ሲከፋኝ ፡ የማዋይህ ፡ ገበናዬን ፡ የማሳይህ
ለክፉ ፡ ቀን ፡ ትሆናለህ ፡ ቢመኩብህ ፡ ታስመካለህ (፪x)

አዝ፦ ከአንተ ፡ በላይ ፡ ለእኔ ፡ የለምና ፡ ለእኔ
አንስቼ ፡ አልጠግብህም ፡ ኢየሱስ ፡ መድህኔ
ከአንተ ፡ በላይ ፡ ለእኔ ፡ የለምና ፡ ለእኔ
አውርቼ ፡ አልጠግብህም ፡ ኢየሱስ ፡ መድህኔ

ሁሉም ፡ እርቆ ፡ ጀርባ ፡ ሲሰጠኝ
ተስፋዬ ፡ ያልኩት ፡ ድንገት ፡ ሲከዳኝ
ቀና ፡ አደረከኝ ፡ እጆቼን ፡ ይዘህ
ዳግም ፡ አቆምከኝ ፡ እንዲህ ፡ ሸላልመህ
ሲከፋኝ ፡ የማዋይህ ፡ ገበናዬን ፡ የማሳይህ
ለክፉ ፡ ቀን ፡ ትሆናለህ ፡ ቢመኩብህ ፡ ታስመካለህ (፪x)

አዝ፦ ከአንተ ፡ በላይ ፡ ለእኔ ፡ የለምና ፡ ለእኔ
አንስቼ ፡ አልጠግብህም ፡ ኢየሱስ ፡ መድህኔ
ከአንተ ፡ በላይ ፡ ለእኔ ፡ የለምና ፡ ለእኔ
አውርቼ ፡ አልጠግብህም ፡ ኢየሱስ ፡ መድህኔ

ቀን ፡ የጣለውን ፡ እዩት ፡ ይሄን ፡ ሰው
ብለው ፡ ሲያወሩ ፡ መነሻም ፡ የለው
ለክፉ ፡ ቀን ፡ ነህ ፡ መኩሪያ ፡ መከታ
እያዩኝ ፡ ወጣሁ ፡ ወደ ፡ ከፍታ
ሲከፋኝ ፡ የማዋይህ ፡ ገበናዬን ፡ የማሳይህ
ለክፉ ፡ ቀን ፡ ትሆናለህ ፡ ቢመኩብህ ፡ ታስመካለህ (፪x)

አዝ፦ ከአንተ ፡ በላይ ፡ ለእኔ ፡ የለምና ፡ ለእኔ
አንስቼ ፡ አልጠግብህም ፡ ኢየሱስ ፡ መድህኔ
ከአንተ ፡ በላይ ፡ ለእኔ ፡ የለምና ፡ ለእኔ
አውርቼ ፡ አልጠግብህም ፡ ኢየሱስ ፡ መድህኔ