ቀና ፡ አልኩኝ (Qena Alkugn) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Tekeste Getnet 4.jpg


(4)

እወራረዳለሁ
(Eweraredalehu)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2004)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6:12
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

ልጨምር ፡ እንጂ ፡ እኔም ፡ እንዲህ ፡ ልበል
ሸክሜን ፡ ከላዬ ፡ ላረክለኝ ፡ ገለል
ብዙ ፡ ብለውሃል ፡ ወዳጅ ፡ ጓደኞቼ
አይበቃም ፡ ልጨምር ፡ እኔም ፡ ተስማምቼ
መልካምነትህን ፡ ባለኝ ፡ አቅም ፡ ላውራ
ተነግሮ ፡ ባያልቅም ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ ስራ

አዝመልካም ፡ ነህ ፡ ከተባልከው ፡ በላይ (፪x)
ስትሰራ ፡ የሌለብህ ፡ ከልካይ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ሁልጊዜ ፡ ኤልሻዳይ
መልካም ፡ ነህ ፡ ከተባልከው ፡ በላይ ፡ በላይ ፡ በላይ
መልካም ፡ ነህ ፡ ከተባልከው ፡ በላይ
ስትሰራ ፡ የሌለብህ ፡ ከልካይ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ሁልጊዜ ፡ ኤልሻዳይ

ከሳሾቼ ፡ ቀርበው ፡ ሲቀበጣጥሩ
በሆነ ፡ ባልሆነው ፡ ነገር ፡ ሲሽርሩ
ጉልበት ፡ የሚያደክም ፡ ልብንም ፡ የሚያርድ
ነበረ ፡ ቃላቸው ፡ ቅጥርን ፡ የሚንድ
ለልጅህ ፡ እራርተህ ፡ ቁጣህ ፡ በተናቸው
ፍፁም ፡ አልተውከኝም ፡ እንደምኞታቸው
እነሱ ፡ ወደቁ ፡ ተሰነካከሉ
በአንተ ፡ ተደግፌ ፡ አመለጥኩ ፡ ከሁሉ

ቀና ፡ አልኩኝ ፡ ከአንገቴ ፡ የልቤ ፡ ደረሰ
በየዋሁ ፡ ጌታ ፡ እምባዬ ፡ ታበሰ
ያለቀስኩባቸው ፡ እነኛ ፡ ዘመናት
አልፌያቸዋለሁ ፡ በጌታዬ ፡ ብርታት

ቀና ፡ አደረገኝ ፡ ቀና ፡ የልቤ ፡ ደረሰ
በየዋሁ ፡ ጌታ ፡ እምባዬ ፡ ታበሰ
ያለቀስኩባቸው ፡ እነኛ ፡ ዘመናት
አልፌያቸዋለሁ ፡ በጌታዬ ፡ ብርታት

አዝመልካም ፡ ነህ ፡ ከተባልከው ፡ በላይ (፪x)
ስትሰራ ፡ የሌለብህ ፡ ከልካይ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ሁልጊዜ ፡ ኤልሻዳይ
መልካም ፡ ነህ ፡ ከተባልከው ፡ በላይ ፡ በላይ ፡ በላይ
መልካም ፡ ነህ ፡ ከተባልከው ፡ በላይ
ስትሰራ ፡ የሌለብህ ፡ ከልካይ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ሁልጊዜ ፡ ኤልሻዳይ

አትገመትም ፡ እንደዚህ ፡ ተብለህ
በሰው ፡ አይምሮ ፡ መቼ ፡ ተመዝነህ
መልካምነትህ ፡ ፍቅርህም ፡ ቢወራ
ተነግሮ ፡ አያልቅም ፡ ሁሉም ፡ በየተራ
እልፍ ፡ ልሳኖች ፡ ሺህ ፡ ቃል ፡ ቢደረደር
ሊገልጥ ፡ አይችልም ፡ ጌታ ፡ የአንተን ፡ ፍቅር

አዝመልካም ፡ ነህ ፡ ከተባልከው ፡ በላይ (፪x)
ስትሰራ ፡ የሌለብህ ፡ ከልካይ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ሁልጊዜ ፡ ኤልሻዳይ
መልካም ፡ ነህ ፡ ከተባልከው ፡ በላይ ፡ በላይ ፡ በላይ
መልካም ፡ ነህ ፡ ከተባልከው ፡ በላይ
ስትሰራ ፡ የሌለብህ ፡ ከልካይ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ሁልጊዜ ፡ ኤልሻዳይ

ቀና ፡ አልኩኝ ፡ ከአንገቴ ፡ የልቤ ፡ ደረሰ
በየዋሁ ፡ ጌታ ፡ እምባዬ ፡ ታበሰ
ያለቀስኩባቸው ፡ እነኛ ፡ ዘመናት
አልፌያቸዋለሁ ፡ በጌታዬ ፡ ብርታት

ቀና ፡ አደረገኝ ፡ ቀና ፡ የልቤ ፡ ደረሰ
በየዋሁ ፡ ጌታ ፡ እምባዬ ፡ ታበሰ
ያለቀስኩባቸው ፡ እነኛ ፡ ዘመናት
አልፌያቸዋለሁ ፡ በጌታዬ ፡ ብርታት