From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ያልሰጠኸኝ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ቀረብኝ ፡ የምለው
እንዴት ፡ ይሄን ፡ ይጠይቅ ፡ ከሞት ፡ የታደከው
ፍላጐቴ ፡ ሞላልኝ ፡ ምኞቴም ፡ ተሳካ
የሁሉ ፡ መደምደሚያ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ለካ
አዝ፦ መጣሁ ፡ ወደ ፡ ደጅህ ፡ ምሥጋና ፡ ልሰጥ
መጣሁ ፡ ወደ ፡ ደጅህ ፡ አምልኮ ፡ ልሰጥ (፪x)
ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ
ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ
ስንፍና ፡ አላወራም ፡ ክፉ ፡ አይወጣም ፡ ከአፌ
ሁሌ ፡ ያስደንቀኛል ፡ ከሞቴ ፡ መትረፌ
ይሄ ፡ ቀረብኝ ፡ ብዬ ፡ አላማህም ፡ ለሰው
ደም ፡ አፍሳሹን ፡ ክፉ ፡ ሰው ፡ ወደህ ፡ ከታደከው
አዝ፦ መጣሁ ፡ ወደ ፡ ደጅህ ፡ ምሥጋና ፡ ልሰጥ
መጣሁ ፡ ወደ ፡ ደጅህ ፡ አምልኮ ፡ ልሰጥ (፪x)
ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ
ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ
ቆም ፡ ብዬ ፡ ሳስበው ፡ የሆነከውን ፡ ለእኔ
ለዘለዓለም ፡ ታደከኝ ፡ ከዚያ ፡ ከኩነኔ
ቀራንዮ ፡ ይናገር ፡ ጐልጐታ ፡ ይመስክር
ለመስቀል ፡ ሞት ፡ አበቃህ ፡ ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር
አዝ፦ መጣሁ ፡ ወደ ፡ ደጅህ ፡ ምሥጋና ፡ ልሰጥ
መጣሁ ፡ ወደ ፡ ደጅህ ፡ አምልኮ ፡ ልሰጥ (፪x)
ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ
ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ
|