ገለበጠው ፡ እንጂ (GelebeTew Enji) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Tekeste Getnet 4.jpg


(4)

እወራረዳለሁ
(Eweraredalehu)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2004)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 4:32
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

ገለበጠው ፡ እንጂ ፡ ድንገት ፡ ጌታ ፡ ደርሶ
ጠላት ፡ ሲጠባበቅ ፡ ጉድጓድ ፡ ለእኔ ፡ ምሶ
ነገር ፡ ሲፈልገኝ ፡ ስፍራ ፡ ለማስለቀቅ
በቆፈረው ፡ ጉድጓድ ፡ እራሱ ፡ ገባበት

አዝ፦ ዘምር ፡ ዘምር ፡ አለኝ
ጠላቴን ፡ ጥሎ ፡ ስላሳየኝ (፪x)

እነኛ ፡ በፈረሳቸው ፡ በሚያልፈው ፡ ነገር ፡ ታመኑ
በሰረጐቻቸው ፡ ብዛት ፡ እጅጉን ፡ ተገዳደሩ
ግን ፡ እንደዋዛ ፡ አለፉ ፡ ተሰነቃቅለው ፡ ወደቁ
የእኔ ፡ ግን ፡ መተማመኛ ፡ አሁንም ፡ አለ ፡ በክብሩ

አዝ፦ ዘምር ፡ ዘምር ፡ አለኝ
ጠላቴን ፡ ጥሎ ፡ ስላሳየኝ (፪x)

በንጉሥ ፡ ደጃፍ ፡ ተጥዬ ፡ ሃማ ፡ ግልምጫው ፡ በርትቶ
ስገድ ፡ ሲለኝ ፡ አልሰግድም ፡ ምንም ፡ ቢያይ ፡ ተቆጥቶ
እጄን ፡ አልሰጥም ፡ ለጠላት ፡ ክፉ ፡ ደግ ፡ በእኔ ፡ ቢያወራ
ቀን ፡ ቆጥሮ ፡ አምላኬ ፡ ይመጣል ፡ ታሪክን ፡ በእኔ ፡ ሊሰራ

አዝ፦ ዘምር ፡ ዘምር ፡ አለኝ
ጠላቴን ፡ ጥሎ ፡ ስላሳየኝ (፪x)

ጠላት ፡ ቢፎክር ፡ ቢያቅራራ ፡ አዋጅ ፡ ቢታወጅ ፡ በእኔ ፡ ላይ
ከቶ ፡ እንዳሰበው ፡ አይሆንም ፡ አምላኬ ፡ እኮ ፡ አለ ፡ በሰማይ
አዋጅን ፡ በአዋጅ ፡ ገልብጦ ፡ ጌታ ፡ መጣና ፡ ቀደመው
ነገሩ ፡ ተገለበጠ ፡ ጠላት ፡ ገባ ፡ በቆፈረው

ገለበጠው ፡ እንጂ ፡ ድንገት ፡ ጌታ ፡ ደርሶ
ጠላት ፡ ሲጠባበቅ ፡ ጉድጓድ ፡ ለእኔ ፡ ምሶ
ነገር ፡ ሲፈልገኝ ፡ ስፍራ ፡ ለማስለቀቅ
በቆፈረው ፡ ጉድጓድ ፡ እራሱ ፡ ገባበት

አዝ፦ ዘምር ፡ ዘምር ፡ አለኝ
ጠላቴን ፡ ጥሎ ፡ ስላሳየኝ (፪x)