ኢየሱስ ፡ ጌታ (Eyesus Gieta) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Tekeste Getnet 4.jpg


(4)

እወራረዳለሁ
(Eweraredalehu)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2004)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 5:24
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

የኃያላን ፡ ቀስት ፡ ተሰባብሮ
አለቅነትን ፡ ስልጣናትን ፡ ሽሮ
በግርማው ፡ ያለ ፡ ሁሉን ፡ እየረታ
ዛሬም ፡ ይገዛል ፡ የጌቶች ፡ ጌታ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ጀግና ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ጀግና ፡ ኢየሱስ

ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ታላቅ ፡ ሥም ፡ አለው
መንግሥቱም ፡ ጽኑ ፡ ነው ፡ ማንም ፡ አይረታው
የተነሱበትን ፡ ሁሉንም ፡ ገልብጦ
ብቻውን ፡ ይገዛል ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ጸንቶ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ

ጐርደድ ፡ እያለ ፡ ከጠላት ፡ ሰፈር
ሺ ፡ ጦር ፡ ቢሰለፍ ፡ የማይበገር
ድምጹ ፡ ነጐድጓድ ፡ የሚያስፈራራ
ሁሉን ፡ የረታ ፡ ተራ ፡ በተራ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ጀግና ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ጀግና ፡ ኢየሱስ

ነጉሰ ፡ ነገሥት ፡ ግርማዊ ፡ ተብለው
በምድር ፡ ሲኖሩ ፡ ክብርን ፡ ተጋፍተው
ዛሬ ፡ ተረስተው ፡ አፈር ፡ ሆነዋል
ሞትን ፡ ፈንቅሎ ፡ ኢየሱስ ፡ ግን ፡ ተነስቷል

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ጀግና ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ጀግና ፡ ኢየሱስ

ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ታላቅ ፡ ሥም ፡ አለው
መንግሥቱም ፡ ጽኑ ፡ ነው ፡ ማንም ፡ አይረታው
የተነሱበትን ፡ ሁሉንም ፡ ገልብጦ
ብቻውን ፡ ይገዛል ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ በልጦ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ (፪x)