From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
እስኪ ፡ ልነሳ ፡ ልሂድ ፡ ልያዘው
ተራራማው ፡ ምድር ፡ የእኔው ፡ እኮ ፡ ነው
እርጅና ፡ አያውቀኝ ፡ እድሜ ፡ አይወስነኝ
ዛሬም ፡ እንደጥንቱ ፡ ጉልበታም ፡ ሰው ፡ ነኝ
ልቤ ፡ አ ይደነግጥ ፡ ሁኔታን ፡ አይቶ
ለውጥን ፡ ያመጣል ፡ ጫካ ፡ ውስጥ ፡ ገብቶ
ልቤ ፡ አይደነግጥ ፡ ሁኔታን ፡ አይቶ
ይመነጥራል ፡ ጫካ ፡ ውስጥ ፡ ገብቶ
አዝ፦ አልሰማም ፡ የጠላትን ፡ ዛቻ
እሄዳለሁ ፡ እስከምድር ፡ ዳርቻ
ሰጥቶኛል ፡ ጌታዪ ፡ ከፋፍቶ
ከፊቴ ፡ ማንስ ፡ ሊቆም ፡ ከቶ
አልሰጋም ፡ በጠላቴ ፡ ዛቻ
እሄዳለሁ ፡ እስከምድር ፡ ዳርቻ
ሰጥቶኛል ፡ ጌታዬ ፡ ከፋፍቶ
ከፊቴ ፡ ማንስ ፡ ሊቆም ፡ ከቶ
እልፍ ፡ ልበል ፡ ልሂድ ፡ ልተወው
የደከምኩበትን ፡ ከተመኘኸው
አልሟገትም ፡ የእኔ ፡ ነው ፡ ብዬ
ፈቀቅ ፡ ልበል ፡ መብቴን ፡ ጥዬ
በፊቴ ፡ ወጥቷል ፡ የሚዋጋልኝ
በእርሱ ፡ ላይ ፡ ጥዬ ፡ እወጣለሁኝ
የአባቶች ፡ አምላክ ፡ ላያሳፍረኝ
ርሆቦት ሆኖ፡ በምድር ፡ አሰፋኝ
አዝ፦ አልሰማም ፡ የጠላትን ፡ ዛቻ
እሄዳለሁ ፡ እስከምድር ፡ ዳርቻ
ሰጥቶኛል ፡ ጌታዬ ፡ ከፋፍቶ
ከፊቴ ፡ ማንስ ፡ ሊቆም ፡ ከቶ
አልሰጋም ፡ በጠላቴ ፡ ዛቻ
እሄዳለሁ ፡ እስከምድር ፡ ዳርቻ
ሰጥቶኛል ፡ ጌታዬ ፡ ከፋፍቶ
ከፊቴ ፡ ማንስ ፡ ሊቆም ፡ ከቶ
እስኪ ፡ ልነሳ ፡ ልሂድ ፡ ልያዘው
ተራራማው ፡ ምድር ፡ የእኔው ፡ እኮ ፡ ነው
እርጅና ፡ አያውቀኝ ፡ እድሜ ፡ አይወስነኝ
ዛሬም ፡ እንደጥንቱ ፡ ጉልበታም ፡ ሰው ፡ ነኝ
ልቤ ፡ አይደነግጥ ፡ ሁኔታን ፡ አይቶ
ለውጥን ፡ ያመጣል ፡ ጫካ ፡ ውስጥ ፡ ገብቶ
ልቤ ፡ አይደነግጥ ፡ ሁኔታን ፡ አይቶ
ይመነጥራል ፡ ጫካ ፡ ውስጥ ፡ ገብቶ
አዝ፦ አልሰማም ፡ የጠላትን ፡ ዛቻ (አልሰማም)
እሄዳለሁ ፡ እስከምድር ፡ ዳርቻ (እሄዳለሁ)
ሰጥቶኛል ፡ ጌታዬ ፡ ከፋፍቶ
ከፊቴ ፡ ማንስ ፡ ሊቆም ፡ ከቶ
አልሰጋም ፡ በጠላቴ ፡ ዛቻ (እሄዳለሁ)
እሄዳለሁ ፡ እስከምድር ፡ ዳርቻ
ሰጥቶኛል ፡ ጌታዬ ፡ ከፋፍቶ
ከፊቴ ፡ ማንስ ፡ ሊቆም ፡ ከቶ
ሰምቶ ፡ በእሳት ፡ የሚመልሰው
እርሱ ፡ አምላክ ፡ ተብሎ ፡ ይጠራ
ክርክር ፡ አላውቅበትም
ጊዜ ፡ አልወስድም ፡ ከእናንተ ፡ ጋራ
እጮሃለሁ ፡ ዛሬ ፡ እንደጥንቱ
ይሰማኛል ፡ ስለው ፡ አቤቱ
መሰዊያው ፡ ላይ ፡ በእሳት ፡ ተገልጦ
ይኸው ፡ ይታይ ፡ እርሱ ፡ ከፍ ፡ ብሎ (፪x)
እወራረዳለሁ ፡ በአምላኬ ፡ በሰማይ ፡ ባለው
እወራረዳለሁ ፡ የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ ታማኝ ፡ ነው
እወራረዳለሁ ፡ ቀኑ ፡ አያልቅም/አያልፍም ፡ ጌታ ፡ ሳይታይ
እወራረዳለሁ ፡ አማላኬ ፡ ነው ፡ በምድር ፡ በሰማይ (፪x)
|