እንኳን ፡ ደስ ፡ አላችሁ (Enkuan Des Alachehu) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Tekeste Getnet 4.jpg


(4)

እወራረዳለሁ
(Eweraredalehu)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2004)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 5:12
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

የፍቅር ፡ አምላክ ፡ የሰላም ፡ ባለቤት
ቸርነቱን ፡ እርሱ ፡ ይጨምርበት
በሃዘንም ፡ ሆነ ፡ በደስታ
አይለያችሁ ፡ ይህ ፡ ቸሩ ፡ ጌታ (፪x)

ፍቅር ፡ ይሁን ፡ በመሃከላችሁ
ሰላም ፡ ይሁን ፡ በመሃከላችሁ
ደስታ ፡ ይሁን ፡ በመሃከላችሁ
እረፍት ፡ ይሁን ፡ በመሃከላችሁ

አዝ፦ እንኳን ፡ ደስ ፡ አላችሁ (፬x)
ይህንን ፡ ውሳኔ ፡ በመወሰናችሁ
የፍቅር ፡ የሰላም ፡ ይሁን ፡ ጋብቻችሁ
እኛ ፡ ደስ ፡ ብሎናል
እንኳን ፡ ደስ ፡ አላችሁ (፪x)

ፀጋ ፡ በረከት ፡ ይሙላ ፡ በቤታችሁ
ሰላም ፡ ጤንነት ፡ ሁሌ ፡ አይለያችሁ
ምንም ፡ አትጡ ፡ ጐዶላችሁ ፡ ይሙላ
ሁልጊዜ ፡ ኑሩ ፡ በፍቅር ፡ በተድላ (፪x)

ፍቅር ፡ ይሁን ፡ በመሃከላችሁ
ሰላም ፡ ይሁን ፡ በመሃከላችሁ
ደስታ ፡ ይሁን ፡ በመሃከላችሁ
እረፍት ፡ ይሁን ፡ በመሃከላችሁ

አዝ፦ እንኳን ፡ ደስ ፡ አላችሁ (፬x)
ይህንን ፡ ውሳኔ ፡ በመወሰናችሁ
የፍቅር ፡ የሰላም ፡ ይሁን ፡ ጋብቻችሁ
እኛ ፡ ደስ ፡ ብሎናል
እንኳን ፡ ደስ ፡ አላችሁ (፪x)