በቃ ፡ በለው (Beqa Belew) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Tekeste Getnet 4.jpg


(4)

እወራረዳለሁ
(Eweraredalehu)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2004)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 4:06
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

ጐበስ ፡ ቀና ፡ ብለህ ፡ ያኔ ፡ በአምሳልህ ፡ የፈጠርከው
አልተገኘም ፡ በስፍራው ፡ ሆኖ ፡ አንተ ፡ እንዳስቀመጥከው
በምኞት ፡ ተሳበ ፡ ወደቀ ፡ በጠላት ፡ ተረታ
እራሱን ፡ በራሱ ፡ በደለ ፡ መቅሰፍትን ፡ አመጣ
የተፍገመገመ ፡ እንዳይወድቅ ፡ መድኃኒት ፡ ላክለት
እንደማይችል ፡ አውቅህ ፡ እንዲሁ ፡ ምህረት ፡ አድርግለት

አዝ፦ በቃ ፡ በለው ፡ እስኪ ፡ ማረው
እንዲህ ፡ ተቅበዝብዟል ፡ በአምሳልህ ፡ የፈጠርከው
በቃ ፡ በለው ፡ እስኪ ፡ ማረው
እንዲህ ፡ ተብቀንቅኗል ፡ በአምሳልህ ፡ የፈጠርከው

ፍጥረት ፡ ተቀሰፈ ፡ አለቀ ፡ እንዲሁ ፡ በከንቱ
እሮሮና ፡ ሃዘን ፡ ያሰማል ፡ ሁሉም ፡ በየቤቱ
ልጆች ፡ አዋቂዎች ፡ ሳይባል ፡ አዛውንቶች ፡ ሁሉ
ያለአጋዥ ፡ ያለጧሪ ፡ ቀርተው ፡ ጐዳናውን ፡ ሁሉ ፡ ሞሉ
ተንከራታቹን ፡ ሰው ፡ አስበው ፡ ልቡን ፡ መልስለት
ረሃብ ፡ ቸነፈር ፡ በሽታውን ፡ አንተ ፡ አስወግድለት

አዝ፦ በቃ ፡ በለው ፡ እስኪ ፡ ማረው
እንዲህ ፡ ተቅበዝብዟል ፡ በአምሳልህ ፡ የፈጠርከው
በቃ ፡ በለው ፡ እስኪ ፡ ማረው
እንዲህ ፡ ተብቀንቅኗል ፡ በአምሳልህ ፡ የፈጠርከው

እረ ፡ ይቅር ፡ በለን ፡ ጩኸታችን ፡ ይውጣ
የሚያግዝ ፡ የለም ፡ ወይ ፡ እንዲህ ፡ ስንቀጣ
ወዴት ፡ አቤት ፡ እንበል ፡ ለማን ፡ እንንገረው
ፍጥረት ፡ ተቅበዝብዟል ፡ አጋዥ ፡ እንደሌለው

ከነገሥታት ፡ መፍትሄ ፡ ጠፍቷል
ከጠቢባን ፡ ጥበብ ፡ ተሰውሯል
አቅም ፡ ያለው ፡ ለውጥን ፡ የሚያመጣ
አንድም ፡ የለም ፡ ሚያድነን ፡ ከቁጣ
አንተ ፡ ግን ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነህና
የሚሳንህ ፡ ምንም ፡ የለምና
አግዘው ፡ እንጂ ፡ ተመልከተው
ይሄ ፡ ፍጥረት ፡ ካለአንተ ፡ ማን ፡ አለው

አዝ፦ በቃ ፡ በለው ፡ እስኪ ፡ ማረው
እንዲህ ፡ ተቅበዝብዟል ፡ በአምሳልህ ፡ የፈጠርከው
በቃ ፡ በለው ፡ እስኪ ፡ ማረው
እንዲህ ፡ ተብቀንቅኗል ፡ በአምሳልህ ፡ የፈጠርከው