በአንተ ፡ አልፌ (Bante Alefie) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Tekeste Getnet 4.jpg


(4)

እወራረዳለሁ
(Eweraredalehu)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2004)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 6:49
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

መቼ ፡ ዘነጋሁት ፡ የትላንቱን ፡ ነገር
ከሞት ፡ የመትረፌ ፡ አያልቅም ፡ ቢነገር
በአደባባይ ፡ ልቁም ፡ የአረከውን ፡ ላውራ
የት ፡ እደርስ ፡ ነበረ ፡ ባልሆን ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፪x)

አዝ፦ ትላንትን ፡ በአንተ ፡ አልፌ
ከጨካኙ ፡ ከአውሬው ፡ ተርፌ
ሳልሰጋ ፡ ልኑር ፡ በደጅህ
ለዛሬም ፡ ትምክቴ ፡ አንተው ፡ ነህ (፪x)

ጌታ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ለእኔ ፡ የለም (፫x)
ጌታ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ለእኔ ፡ የለም (፫x)

የፀሐዩን ፡ ብርታት ፡ በጥላ ፡ ከልለህ
ድቅድቁን ፡ ጨለማ ፡ በብርሃን ፡ ለውጠህ
ቁር ፡ ሳያገኘኝ ፡ እባቡ ፡ ሳይነድፈኝ
አቤት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ከስንቱ ፡ ታደከኝ (፪x)

አዝ፦ ትላንትን ፡ በአንተ ፡ አልፌ
ከጨካኙ ፡ ከአውሬው ፡ ተርፌ
ሳልሰጋ ፡ ልኑር ፡ በደጅህ
ለዛሬም ፡ ትምክቴ ፡ አንተው ፡ ነህ (፪x)

ትዝ ፡ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ያረክልኝ ፡ ሁሉ
ሳልቆጥብ ፡ ልናገር ፡ ዘመኔን ፡ በሙሉ
ጌታ ፡ ማዳንህን ፡ ለሰው ፡ ሳላወራ
አንድም ፡ ቀን ፡ አያልፍም ፡ ስምህን ፡ ሳልጠራ (፪x)

አዝ፦ ትላንትን ፡ በአንተ ፡ አልፌ
ከጨካኙ ፡ ከአውሬው ፡ ተርፌ
ሳልሰጋ ፡ ልኑር ፡ በደጅህ
ለዛሬም ፡ ትምክቴ ፡ አንተው ፡ ነህ (፪x)