Tekeste Getnet/Eweraredalehu/Alesham

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ተከስተ ጌትነት ርዕስ አልሻም አልበም እወራረዳለሁ

አዝ አልሻም ሌላ ሌላ ነገር ምኞቴ አንተን ብቻ ማክበር የበላይ ሆነህ በሕይወቴ ያንግስህ መላው እኔነቴ (፪x)

ሌላውማ ሌላውማ ከአንተ ውጪ ሌላ ሌላውማ ገብቶኛል ለእኔ እንደማይስማማ (፪x) አየሁት ለእኔ እንደማይስማማ (፪x)

ዓይኔን አንስቼ ከሌላው ላይ ሾምኩህ ጌታዬ በልቤ ላይ ግራ ቀኝ ብልም አያምርብኝም ያለአንተ ለእኔስ አይሆንልኝም እርካታዬ ነህ (፫x) እርካታዬ ነህ ወግ ማዕረጌ ነህ (፫x) ወግ ማዕረጌ ነህ

አዝ አልሻም ሌላ ሌላ ነገር ምኞቴ አንተን ብቻ ማክበር የበላይ ሆነህ በሕይወቴ ያንግስህ መላው እኔነቴ (፪x)

ሌላውማ ሌላውማ ከአንተ ውጬ ሌላ ሌላውማ ገብቶኛል ለእኔ እንደማይስማማ (፪x) አየሁት ለእኔ እንደማይስማማ (፪x)

ልቤ ፅኑ ነው ተማመንኩብህ ዘመኔን ለአንተ ይሄው ሰጠሁህ ምራኝ ጌታዬ ወደ ወደድከው እኔነት የለኝ ሁሉ የአንተ ነው እርካታዬ ነህ (፫x) እርካታዬ ነህ ወግ ማዕረጌ ነህ (፫x) ወግ ማዕረጌ ነህ

አዝ አልሻም ሌላ ሌላ ነገር ምኞቴ አንተን ብቻ ማክበር የበላይ ሆነህ በሕይወቴ ያንግስህ መላው እኔነቴ

ያሰብኩት ባይሆን የተመኘሁት ሰላሜ በዛ በአንተ ያገኘሁት አላማርርም ይሁን ያሰብከው አላማህ ለእኔ ሁሌም በጐ ነው እርካታዬ ነህ (፫x) እርካታዬ ነህ ወግ ማዕረጌ ነህ (፫x) ወግ ማዕረጌ ነህ

አዝ አልሻም ሌላ ሌላ ነገር ምኞቴ አንተን ብቻ ማክበር የበላይ ሆነህ በሕይወቴ ያንግስህ መላው እኔነቴ (፪x)

ሌላውማ ሌላውማ ከአንተ ውጪ ሌላ ሌላውማ ገብቶኛል ለእኔ እንደማይስማማ (፪x) አየሁት ለእኔ እንደማይስማማ (፪x)