ሰው ከንቱ (Sew Kentu) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Tekeste Getnet 5.jpg


(5)

Deg Neh
(Deg Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2008)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:28
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

ባጎረሰ የተነከሰ በቤቱ አለ ስንቱ እያለቀሰ
ለክፉ ቀን ነበረ ወዳጁ ግን ተገኘ ሲሸምት እደጁ
ከገበታው ላይ የበላ ተረከዙን ደግሞ ቢያነሳ
ለትምህርት ተፅፏል በቃሉ ገሮች ሆይ ይህንን ልብ በሉ
ሳዖል አስተካክሎ ስል ጦሩን ወረወረ ሊገል ዳዊትን
አምላክ አተረፈው ገብቶ ጣልቃ የወንድምም ክፉ አለ ለካ

ይቅር አይወራ ክፉም አትናገር
ልመድልኝ ልቤ ሁሉን ችሎ ማደር
ጉድጓዱን የሚምስ ራሱ ሊወድቅበት
ግዜ እስኪያስተምረው አንተ አትፍረድበት

ይሁን አይወራ ክፉን አትናገር
ልቤ አስተውል ልቤ ሁሉን ችሎ ማደር
ጉድጓዱን የሚምስ ራሱ ሊወድቅበት
ግዜ አለው ለሁሉ ተው አትፍረድበት

ሰው ከንቱ/3 መሆኑን ተረዳው ሰው ከንቱ
ሰው ከንቱ/3 መሆኑን ገብቶኛል ሰው ከንቱ

ቢጠበብ ከንቱ ከንቱ ከንቱ
ቢያስተውል ከንቱ ከንቱ ከንቱ
ጌታ ካልረዳው ከንቱ ከንቱ
ልቡን ካልያዘው ከንቱ ከንቱ

መሰዋቱን ጌታ ችላ ቢለው ተቆጥቶ ወንድሙን ገደለው
ያድርግ እንጂ እርሱ እንደወደደ አንዱን ትቶ አንዱን ከመወደደ
ወንድምህን ወዴት አረከው እንዳላየ ሆኖ ቢጠይቀው
አይደለሁም የሱ ጠባቂ ብሎ መለሰ ያ አላዋቂ
ደሙ ጮክ ብሎ አወራ ያለበደል ምነው ግፍ ተሰራ
ተንከራታች ሆነ በምድር ላይ እግዚአብሔር አይቷል ሰው ባያይ

ሰው ከንቱ/3 መሆኑን ተረዳው ሰው ከንቱ
ሰው ከንቱ/3 መሆኑን ገብቶኛል ሰው ከንቱ

ቢያገኝም ከንቱ ከንቱ ከንቱ
ባያገኝ ከንቱ ከንቱ ከንቱ
ጌታ ካልረዳው ከንቱ ከንቱ
ልቡን ካልያዘው ከንቱ ከንቱ