ሰማይን ፡ የሰራ (Semayen Yesera) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)


(5)

ደግ ፡ ነህ
(Deg Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2008)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:05
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

ከሰማያት ፡ በላይ ፡ ያለኸው
እረድኤታችን ፡ የሆንከው
ከደመናት ፡ በላይ ፡ ተራምደሃል
እግዚአብሔር ፡ ማንስ ፡ ይመስልሃል (፪x)

ማነው ፡ ሰማይን ፡ የሰራ
ማነው ፡ ምድርን ፡ ያፀና
ሌላው ፡ ካንተ ፡ በቀር ፡ የለም
ጌታ ፡ ነህ ፡ ክበር ፡ ለዘላለም (፪x)
ጌታ ፡ ክበር ፡ ለዘላለም
ጌታ ፡ ንገስ ፡ ለዘላለም

ይነሳና ፡ እስኪ ፡ ይናገር
አምላክ ፡ ማነው ፡ ከአንተስ ፡ በቀር
በጉልበትህ ፡ ጽናት ፡ ተራምደህ
ትኖራለህ ፡ ሁልጊዜ ፡ ከብረህ (፪x)

ታላቅነትህ ፡ ቢወራ ፡ ቢነገር
ምንም ፡ አይገልጽህ ፡ ከመደነቅ ፡ በቀር (፪x)
እንዲያው ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ ባለኝ ፡ አቅም
ብዬ ፡ ልለፈው ፡ እንዳተ ፡ የለም (፪x)
(እስኪ ፡ ማነው)

ማነው ፡ ሰማይን ፡ የሰራ (የሰራ)
ማነው ፡ ምድርን ፡ ያቀና (ያጸና)
ሌላው ፡ ካንተ ፡ በቀር ፡ የለም (የለም ፡ የለም)
ጌታ ፡ ነህ ፡ ግዛን ፡ ለዘላለም (ለዘላለም) (፪x)
ጌታ ፡ ክበር ፡ ለዘላለም
ጌታ ፡ ንገስ ፡ ለዘላለም (፬x)