ልቤ ፡ ፀና (Lebie Tsena) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Tekeste Getnet 5.jpg


(5)

ደግ ፡ ነህ
(Deg Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2008)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 6:36
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

አዝ፦ ልቤ ፡ ፀና
ልቤ ፡ በአንተ ፡ ፀና (፪x)

ቃልህን ፡ ይዣለሁ ፡ ባይታይ ፡ ደመና
ዘምር ፡ ዘምር ፡ አለኝ ፡ ልቤ ፡ በአንተ ፡ ፀና

አዝ፦ ልቤ ፡ ፀና
ልቤ ፡ በአንተ ፡ ፀና (፪x)

ሳይቀየር ፡ ሁሉ ፡ እንዳለ ፡ ሆኖ
ሲያመሰግን ፡ በአምላኩ ፡ ተማምኖ
ምድረበዳን ፡ የሚያለመልመው
በረሃውን ፡ ገነት ፡ አደረገው

ሳይቀየር ፡ ሁሉ ፡ እንዳለ ፡ ሆኖ
ሲያመሰግን ፡ በአምላኩ ፡ ተማምኖ
ምድረበዳን ፡ የሚያለመልመው
ድንገት ፡ ደርሶ ፡ ታሪኩን ፡ ቀየረው

አዝ፦ ልቤ ፡ ፀና
ልቤ ፡ በአንተ ፡ ፀና (፪x)

ቃልህን ፡ ይዣለሁ ፡ ፡ ባይታይ ፡ ደመና
ዘምር ፡ ዘምር ፡ አለኝ ፡ ልቤ ፡ በአንተ ፡ ፀና

አዝ፦ ልቤ ፡ ፀና
ልቤ ፡ በአንተ ፡ ፀና (፪x)

በገናዬ ፡ ከተሰቀለበት
ይውረድና ፡ ቅኔን ፡ ልቀኝበት
ሁኔታው ፡ ሳይቀያየር
አውቅበት ፡ የለ ፡ ለአንተ ፡ መዘምር

በገናዬ ፡ ከተሰቀለበት
ይውረድ ፡ እንጂ ፡ ቅኔን ፡ ልቀኝበት
ሁኔታው ፡ ሳይቀያየር
አውቅበት ፡ የለ ፡ ለአንተ ፡ መዘምር

ምሥጋና ፡ ለሥምህ
ምሥጋና ፡ ለክብርህ
ይገባሃል ፡ ጌታ
አይጓደለብህ

ዝማሬ ፡ ለሥምህ
ዝማሬ ፡ ለክብርህ
ይገባሃል ፡ አንተስ
አይጓደለብህ

ባያድነን ፡ እኛስ ፡ ለአንተ ፡ አንሰግድም
ላቆመውከው ፡ ምስል ፡ ፈፅሞ ፡ እጅ ፡ አንሰጥም
ሰባት ፡ እጥፍ ፡ ቢነድም ፡ እሳቱ
ይመለካል ፡ የእኛስ ፡ ክንደ ፡ ብርቱ (፪x)

ምሥጋና ፡ ለሥምህ
ምሥጋና ፡ ለክብርህ
ይገባሃል ፡ ጌታ
አይጓደለብህ

ዝማሬ ፡ ለሥምህ
ዝማሬ ፡ ለክብርህ
ይገባሃል ፡ አንተስ
አይጓደለብህ

ባሪያዎችህ ፡ ወህኒ ፡ ቤት ፡ ተጥለው
ግን ፡ ሲያመልኩ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ብለው
የወህኒውን ፡ መሠረት ፡ አናውጠህ
ተገልጠሃል ፡ እስራት ፡ በጣጥሰህ

ቅዱስ (፫x)
ጌታ ፡ ኢየሱስ
ኃያል (፫x)
የሚመስልህ ፡ ታጥቷል (፪x)

አዝ፦ ልቤ ፡ ፀና
ልቤ ፡ በአንተ ፡ ፀና (፫x)