እየሱስ (Eyesus) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Tekeste Getnet 5.jpg


(5)

Deg Neh
(Deg Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2008)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 4:41
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

ትዝ እያለኝ ትውስ እያለኝ
በፃድቃን ጉባኤ ላመልክህ ቆምኩኝ
ትዝ እያለኝ ትውስ እያለኝ
ከሚወዱህ ጋራ ላመልክህ ቆምኩኝ

እየሱስ/8

ቸርነትህ የገባው ባንተ የተጎበኘ
ሊወድስህ ሊያከብርህ ባደባባይ ተገኘ
አልቀረም ቅጭ እንዳለ ከችግሩ ተጣብቆ
ያከብርሃል በሰው ፊት ማቁን ከላዩ አውልቆ

እየሱስ/8

ወዳንተ የማጣውን ሁሉን ደህና አድርገህ
አቀርቅሮ እንዳይመለስ ቀንበሩን ትሰብራለህ
መፍትሄ ከታጣለት ተስፋ ከሌለው ጉዳይ
እፎይ አለ ስንቱ ሰው ሆነህለት ገላጋይ

እውራን አይተዋል እየሱስ
ለምፃሞችም ነፁ እየሱስ
አንካሶች ዘለዋል እየሱስ
ሙታንም ተነሱ እየሱስ
ክንድህ አልደከመ እየሱስ
ሁሌም ትሰራለህ እየሱስ
ትላንትናም ዛሬም እየሱስ
ዘላለም ህያው ነህ እየሱስ

ስላንተማ ይወራ ስላንተማ ይነገር
ለጭኩኑ ባትደርስ እንዴትስ ይሆን ነበር
ውሎ አደረ በሰላም ምህረትህን ተማምኖ
ክብር ያየ በቤትህ አይጠግብም አመስግኖ

እየሱስ/8

ትዝ እያለኝ ትውስ እያለኝ
በፃድቃን ጉባኤ ላመልክህ ቆምኩኝ
ትዝ እያለኝ ትውስ እያለኝ
ከሚወዱህ ጋራ ላመልክህ ቆምኩኝ