እንዳገና (Endegena) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Tekeste Getnet 5.jpg


(5)

Deg Neh
(Deg Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2008)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 5:03
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

የእንደገና አምላክ ነህ የእንደገና
የሱ ነገር በቃኝ መች ትልና
ተቆጥተህ ማንንም አልጣልክም
እሩሩ ነህ ትወዳለህ ዳግም

ስንፍና ዙሩያውን ቢከበው
ተነሳ ብረር ብረር አለው
ተመኘ ሊሆን እንደልቡ
ነጎደ ወደመራው ቀልቡ
አልሆነው ሁሉም እንዳሰበው
ከእሪያ ጋራ በላ ቢርበው
ቢቆጨው መጣ ወደ ቤትህ
አቀፍከው አልጠቆረም ፊትህ

እንደገና ራራህለት እንደገና አዘንክለት/2

ጨክኖ ሁሉም ሰው ቢተውህ
እስከሞት እኔ ግን አለሁህ
ያለው ሰው ደጋግሞ እየማለ
ሶስት ግዜ አላውቅህም አለ
ይህማ ከእየሱስ ጋር ነበር
ይመስላል ሲያወራ ሲናገር
ጠየቁት ብለው ከወዴት ነህ
እርሱ ግን በገረድ ፊት ካደህ

እንደገና ራራህለት እንደገና አዘንክለት/2

የእንደገና አምላክ ነህ የእንደገና
የሱ ነገር በቃኝ መች ትልና
ተቆጥተህ ማንንም አልጣልክም
እሩሩ ነህ ትወዳለህ ዳግም

ያቺም ሴት ስትዘሙት ተገኝታ
አመጧት ከላህበት ቦታ
ይውገራት ሃጥያት የሌለበት
አልካቸው ሳያስቡት ድንገት
ቆም ብለው ራሳቸውን ሲያዩ
ያው ናቸው ከሱዋ ያልተለዩ
አንድባንድ ከፊት ህ እራቁ
የአንተን ፀጋ እያደነቁ

እንደገና ራራህላት እንደገና አዘንክላይ/2