ደግ ፡ ነህ (Deg Neh) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Tekeste Getnet 5.jpg


(5)

ደግ ፡ ነህ
(Deg Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2008)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 7:02
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

እንዲህ ፡ ያለ ፡ መውደድ ፡ ከቃላት ፡ ያለፈ
ስለጠላቶቹ ፡ ነፍሱን ፡ ያሳለፈ
ፍጥረት ፡ በሙሉ ፡ ተደንቆ ፡ ዋለ
ፍቅር ፡ እንዳንተ ፡ የለም ፡ እያለ
ፀሐይም ፡ አለች ፡ ብርሃን ፡ ለምኔ
መስቀል ፡ ላይ ፡ ሲውል ፡ ደጉ ፡ መድህኔ

አዝ፦ ባህሪህ ፡ ባህሪህ ፡ ቢደንቃቸው ፡ ደግ ፡ ነህ ፡ አሉህ
ባህሪህ ፡ ባህሪህ ፡ ቢያስገርመኝ ፡ ደግ ፡ ነህ ፡ አልኩህ

ወደ ፡ ሙት ፡ ሲነዳ (ደግ ፡ ነህ)
የአዳም ፡ ዘር ፡ በሙሉ (ደግ ፡ ነህ)
ሞቱን ፡ ሞተህለት (ደግ ፡ ነህ)
ደርሰህ ፡ ካለህ ፡ ሁሉ (ደግ ፡ ነህ)
ነፍስን ፡ እስከመስጠት (ደግ ፡ ነህ)
ፍቅርህ ፡ ተፈትኖ (ደግ ፡ ነህ)
ከፍርድ ፡ አመለጠ (ደግ ፡ ነህ)
ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ሆኖ (ደግ ፡ ነህ)

አዝ፦ ባህሪህ ፡ ባህሪህ ፡ ቢደንቃቸው ፡ ደግ ፡ ነህ ፡ አሉህ
ባህሪህ ፡ ባህሪህ ፡ ቢያስገርመኝ ፡ ደግ ፡ ነህ ፡ አልኩህ

ለፃድቅ ፡ የሚሞት ፡ በጭንቅ ፡ ከተገኘ
አጥቶ ፡ ተስፋ ፡ ቆርጦ ፡ መኖር ፡ ባልተመኘ
ግን ፡ ተገለጠ ፡ ፍቅር ፡ ለሁሉ
አመለጡብህ ፡ ጌታን ፡ እያሉ
ለየት ፡ ያለ ፡ ነው ፡ ያንተስ ፡ ፍቅር
መሰከሩልህ ፡ ሰማይ ፡ ምድር ፡

አዝ፦ ባህሪህ ፡ ባህሪህ ፡ ቢደንቃቸው ፡ ደግ ፡ ነህ ፡ አሉህ
ባህሪህ ፡ ባህሪህ ፡ ቢያስገርመኝ ፡ ደግ ፡ ነህ ፡ አልኩህ

አቅም ፡ አጥተህ ፡ አይደል ፡ ተሸንፈህ
በጨካኞች ፡ ጡንቻ ፡ ላይ ፡ መውደቅህ
እንደሚታረድ ፡ በግ ፡ እየነዱ
በመስቀል ፡ ሊገሉህ ፡ ወደዱ (፪x)

አዝ፦ ባህሪህ ፡ ባህሪህ ፡ ቢደንቃቸው ፡ ደግ ፡ ነህ ፡ አሉህ
ባህሪህ ፡ ባህሪህ ፡ ቢያስገርመኝ ፡ ደግ ፡ ነህ ፡ አልኩህ

አወይ ፡ አጨካከን ፡ ጠፍቶ ፡ የሚራራ
እያወካከቡ ፡ ነዱት ፡ በተራራ
አፉ ፡ አልተከፈተ ፡ ክፉ ፡ አልተናገረ
ጭራሽ ፡ ለሚጠሉት ፡ ይማልድ ፡ ጀመረ

ወዶ ፡ አለም ፡ ቢያወድሰው
በእርግጥ ፡ ስለሚገባው ፡ ነው
ለእኛ ፡ ብሎ ፡ ታርዷል ፡ እና
ለእርሱ ፡ ይገባል ፡ ምስጋና (፪x)