አማን አይደለም ወይ (Aman Aydelem Wey) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Tekeste Getnet 5.jpg


(5)

Deg Neh
(Deg Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2008)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:17
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

ይህንን ተግዳሮት ለሚያርቅለት
ንጉስ ቃሉን ሰጠ ልጁን ሊድርለት
ግብር እንዳይከፍል ይሁን ባለፀጋ
እጅ መንሻ ይኸው ደፍሮ ለሚዋጋ

ሽልማቱም ይቅር ከሱ የለም ልቤ
አምላኬ እንዲገለጥ ነው የኔ ሃሳቤ
እጅ መንሻው ይቅር ከሱ የለም ልቤ
አምላክ አለ ይባል ይሄ ነው ሃሳቤ

አማን አይደለም ወይ ከተማው መንደሩ
የወገኔ ልጆች ምነው ተሸበሩ
ይሄ ያልተገረዘ ከሆነ ሚያስጨንቅ
ባምላክ ስም ልግጠመው ማንም ልቡ አይውደቅ

ሰላም አይደለም ወይ ከተማው መንደሩ
የእስራኤል ልጆች ምነው ተሸበሩ
ይሄ ያልተገረዘ ከሆነ ሚያስጨንቅ
ባምላክ ስም ልግጠመው ማንም ልቡ አይውደቅ

ሆ ብሎ ወጣ እንደቀደመው
ደሞ መዋጋት እስራኤል ልምድ አለው
ይዛሬው ውጊያ አንድ ለአንድ
ማነው ሚገጥመኝ ብሎ ሲንጎራደድ

ደግሞ ፎከረ ጎልያድ በያደባባዩ
ታላላቆችን ጭጭ አሉ አይተው እንዳለዩ
ግን ምድረበዳ በግሉ አምላኩን ያወቀ
እገጥማለሁኝ ብሎ ወገቡን ታጠቀ

አማን አይደለም ወይ ከተማው መንደሩ
የወገኔ ልጆች ምነው ተሸበሩ
ይሄ ያልተገረዘ ከሆነ ሚያስጨንቅ
ባምላክ ስም ልግጠመው ማንም ልቡ አይውደቅ

ሰላም አይደለም ወይ ከተማው መንደሩ
የእስራኤል ልጆች ምነው ተሸበሩ
ይሄ ያልተገረዘ ከሆነ ሚያስጨንቅ
ባምላክ ስም ልግጠመው ማንም ልቡ አይውደቅ

እንደልማዱ ከሰልፉ መሃል
ቆሞ ሲናገር ልብን ያቀልጣል
ከእስራኤል ወገን ጠፍቶ ሚገጥመው
ሲረበሽ ዋለ አቤት ስንቱ ሰው

ደግሞ ፎከረ ጎልያድ በያደባባዩ
ታላላቆችን ጭጭ አሉ አይተው እንዳለዩ
ግን ምድረበዳ በግሉ አምላኩን ያወቀ
እገጥማለሁኝ ብሎ ወገቡን ታጠቀ

አማን አይደለም ወይ ከተማው መንደሩ
የወገኔ ልጆች ምነው ተሸበሩ
ይሄ ያልተገረዘ ከሆነ ሚያስጨንቅ
ባምላክ ስም ልግጠመው ማንም ልቡ አይውደቅ

ሰላም አይደለም ወይ ከተማው መንደሩ
የእስራኤል ልጆች ምነው ተሸበሩ
ይሄ ያልተገረዘ ከሆነ ሚያስጨንቅ
ባምላክ ስም ልግጠመው ማንም ልቡ አይውደቅ

አምልካክ አለኝ ሚዋጋልኝ
ካንበሳ ከድብ ያስመለጠኝ