From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
እግዚአብሔርን ፡ ቆይቼ ፡ ደጅ ፡ ጠናሁት
ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ እንደሚሆን ፡ ስላመንኩት
እርሱም ፡ ጩኸቴን ፡ ሰምቶ ፡ አዘነልኝ
ዘንበል ፡ አለልኝ ፡ ወደኔ ፡ ዘንበል ፡ አለልኝ (፪x)
ከረግረጉ ፡ ጭቃ ፡ ከጥፋትም ፡ ጉድጓድ
ከአስፈሪው ፡ ጨለማ ፡ ከሰይጣንም ፡ ወጥመድ
አስመለጠን ፡ ጌታ ፡ በዛ ፡ ቸርነቱ
ምርኮዬም ፡ ተመለሰ ፡ አበራልኝ ፡ ፊቱ
አዝ፦ (ቸር ፡ ነው) ፡ ከለመንኩት ፡ በላይ ፡ አብልጦ
(ቸር ፡ ነው) ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ አደረገልኝ
(ቸር ፡ ነው) ፡ ተትረፈረፈልኝ ፡ ምህረቱ
(ቸር ፡ ነው) ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ሆነብኝ
ጩኸቴን ፡ ሰማና ፡ አለሁ ፡ አለኝ ፡ ከሞት ፡ አስጣለኝ
የማይገባኝን ፡ ክብር ፡ አገኘሁ ፡ ልጁ ፡ ተሰኘሁ
በእጆቹ ፡ መዳፍ ፡ ላይ ፡ ቀርጾኛል ፡ ምን ፡ ያስፈራኛል
ምህረትና ፡ ቸርነቱ ፡ ይከተሉኛል
እግዚአብሔርን ፡ ለሚወዱት ፡ እንደሃሳቡም ፡ ለተጠሩት
እንደሚናገር ፡ ቅዱስ ፡ ቃሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው ፡ ነገር ፡ ሁሉ
እግዚአብሔርን ፡ ቆይቼ ፡ ደጅ ፡ ጠናሁት
ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ እንደሚሆን ፡ ስላመንኩት
እርሱም ፡ ጩኸቴን ፡ ሰምቶ ፡ አዘነልኝ
ዘንበል ፡ አለልኝ ፡ ወደኔ ፡ ዘንበል ፡ አለልኝ (፪x)
አልቀረም ፡ በከንቱ ፡ ጩኸት ፡ ልመናዬ
በጊዜው ፡ መለሰልኝ ፡ ታማኙ ፡ ጌታዬ
ውድቀቴን ፡ የሚሹት ፡ አለቀለት ፡ ሲሉ
ለበጐ ፡ አደረገልኝ ፡ መከራዬን ፡ ሁሉ
አዝ፦ (ቸር ፡ ነው) ፡ ቃልኪዳኑን ፡ ከቶ ፡ የማይረሳ
(ቸር ፡ ነው) ፡ የወደቁትን ፡ የሚያነሳ
(ቸር ፡ ነው) ፡ ለታመኑት ፡ የማያሳፍር
(ቸር ፡ ነው) ፡ ከትቢያ ፡ አንስቶ ፡ የሚያከብር
የዘገየ ፡ መስሎ ፡ ሁሌ ፡ ፊት ፡ ይገኛል (፪x)
በሞተው ፡ ነገር ፡ ላይ ፡ ሕይወትን ፡ ይዘራል (፪x)
የጸና ፡ ግንብ ፡ ነው ፡ ለአመኑት ፡ የእርሱ ፡ ሥም ፡ የእግዚአብሔር ፡ ሥም
ወደርሱ ፡ የሮጠ ፡ አፍሮ ፡ አይመለሥም ፡ ከስሮ ፡ አይመለስም
እግዚአብሔርን ፡ ለሚወዱት ፡ እንደሃሳቡም ፡ ለተጠሩት
እንደሚናገር ፡ ቅዱስ ፡ ቃሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው ፡ ነገር ፡ ሁሉ (፪x)
|