ይታመናል (Yetamenal) - ተፈራ ፡ ነጋሽ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ተፈራ ፡ ነጋሽ
(Tefera Negash)

Tefera Negash 1.jpg


(1)

አልመለስም
(Alemelesem)

ዓ.ም. (Year): 2011
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተፈራ ፡ ነጋሽ ፡ አልበሞች
(Albums by Tefera Negash)

ልዑል ፡ ነህ ፡ ተብሎ ፡ በፈርዖን ፡ ቤት
ስፍራው ፡ እንዳልሆነ ፡ ሲገባው ፡ እውነት
ሁሉን ፡ ክብር ፡ ትቶ ፡ መረጠ ፡ መከራ
ተስማማ ፡ ጨክኖ ፡ ከፈጣሪው ፡ ጋራ
(፪x)

በዐይን ፡ ከሚታየው ፡ ይልቅ ፡ የማይታየውን ፡ አምኖ
የዘለዓለም ፡ መታመኛው ፡ መኖሪያው ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆኖ
ተሰደደ ፡ ሁሉን ፡ ትቶ ፡ ችግር ፡ መከራን ፡ ሳይፈራ
በእውነት ፡ አድርጓልና ፡ መንገዱን ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ጋራ

(አመነ ፡ እግዚአብሔርን ፡ አመነ) በትህትና ፡ ታዘዘ
(ለእውነት ፡ ለመታዘዝ ፡ ጨከነ) ወደ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ተጓዘ
(አመነ ፡ እግዚአብሔርን ፡ አመነ) ትኩር ፡ ብሎ ፡ አይቶ ፡ የሩቁን
(ለእውነት ፡ ለመታዘዝ ፡ ጨከነ) የተጠበቀለት ፡ እርስቱን
(አመነ ፡ እግዚአብሔርን ፡ አመነ) በእውነት ፡ እግዚአብሔር ፡ ይታመናል (፬x)

ዛሬም ፡ ዋጋውን ፡ ተምኖ ፡ ከልቡ ፡ ታዛዥ ፡ የሆነ
ከመልካም ፡ ነገር ፡ አይጐድልም ፡ ለአምላኩ ፡ የታመነ
ምንም ፡ ፈተናው ፡ ቢበዛ ፡ የጊዜው ፡ ችግር ፡ መከራ
በአሸናፊነት ፡ ይኖራል ፡ የሕይወት ፡ ፍሬ ፡ እያፈራ

(በእውነት ፡ እግዚአብሔር ፡ ይታመናል) ለጥሪው ፡ ምላሽ ፡ ለሰጠ
(እንዳለው ፡ እንደ ፡ ቃሉ ፡ ያደርጋል) በነፍሱ ፡ ሳይቀር ፡ ለቆረጠ
(በእውነት ፡ እግዚአብሔር ፡ ይታመናል) የድል ፡ አክሊል ፡ ሽልማት
(እንዳለው ፡ እንደ ፡ ቃሉ ፡ ያደርጋል) አይቀርም ፡ በጊዜው ፡ በወቅቱ
(እንዳለው ፡ እንደ ፡ ቃሉ) በእውነት ፡ እግዚአብሔር ፡ ይታመናል (፬x)

በኀጢአት ፡ ከሚገኘው ፡ ደስታ ፡ ይሻላል ፡ ታምኖ ፡ መኖር ፡ በጌታ
የፈርዖንን ፡ ሹመት ፡ ተረድቶ ፡ ተሰደደ ፡ ሙሴ ፡ ክርስቶስን ፡ መርጦ
ምን ፡ ቢበዛ ፡ መከራና ፡ ስደቱ ፡ በሰማይ ፡ የድል ፡ አክሊል ፡ ነው ፡ ሽልማቱ