ፀጋህ ፡ ያግዘኝ (Tsegah Yagzegn) - ተፈራ ፡ ነጋሽ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተፈራ ፡ ነጋሽ
(Tefera Negash)

Tefera Negash 1.jpg


(1)

አልመለስም
(Alemelesem)

ዓ.ም. (Year): 2011
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተፈራ ፡ ነጋሽ ፡ አልበሞች
(Albums by Tefera Negash)

አዝ፦ ፀጋህ ፡ ያግዘኝ ፡ እንጂ
መንፈስህ ፡ ይምራኝ ፡ እንጂ
ምን ፡ አቅም ፡ አለኝ ፡ እኔ
በአንተው ፡ ነው ፡ ሰው ፡ መሆኔ (፪x)

ጌታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ጌታዬ
አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ዋስትናዬ (፪x)

የዘለዓለም ፡ እቅድህን ፡ በእኔ ፡ ያለህን ፡ አላማ ፡
ፈጽሜ ፡ ደስ ፡ እንዳሰኝህ ፡ እርዳኝ ፡ ከሐሳብህ ፡ ልስማማ ።
በሚሰማ ፡ በሚታየው ፡ እንዳልወሰድ ፡ ከቤትህ
ምራኝ ፡ እጆቼን ፡ ያዝና ፡ ሁልጊዜ ፡ ልኑር ፡ በፊትህ (፪x)

እርዳኝ ፡ እንዳላሳዝንህ ፡ እርዳኝ (፫x)
እርዳኝ ፡ በቤትህ ፡ እንድኖር ፡ እርዳኝ

አዝ፦ ፀጋህ ፡ ያግዘኝ ፡ እንጂ
መንፈስህ ፡ ይምራኝ ፡ እንጂ
ምን ፡ አቅም ፡ አለኝ ፡ እኔ
በአንተ ፡ ነው ፡ ሰው ፡ መሆኔ (፪x)

ጌታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ጌታዬ (ጌታዬ)
አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ዋስትናዬ (ዋስትናዬ) (፪x)

እምነት ፡ እንደጐደለው ፡ ሰው ፡ መጠራቴ ፡ እንዳይቀርብኝ ፡
የፈቃድህን ፡ ምሥጢር ፡ እንዳውቅ ፡ ጥበብ ፡ ማስተዋልን ፡ ስጠኝ
ስንፍናዬ ፡ ከኔ ፡ ርቆ ፡ እንዲያምር ፡ መጨረሻዬ
መልካም ፡ ፍሬ ፡ እንዲገኝብኝ ፡ ደግፈኝ ፡ ከመነሻዬ ፡ (፪x)

እርዳኝ (እርዳኝ) ፡ እንዳላሳዝንህ ፡ እርዳኝ (፫x)
እርዳኝ (እርዳኝ) ፡ በቤትህ ፡ እንድኖር ፡ እርዳኝ

አዝ፦ ፀጋህ ፡ ያግዘኝ ፡ እንጂ
መንፈስህ ፡ ይምራኝ ፡ እንጂ
ምን ፡ አቅም ፡ አለኝ ፡ እኔ
በአንተ ፡ ነው ፡ ሰው ፡ መሆኔ (፪x)

ጌታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ጌታዬ (ጌታዬ)
አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ዋስትናዬ (ዋስትናዬ) (፪x)