ቃል ፡ ነው ፡ መሠረቴ (Qal New Meseretie) - ተፈራ ፡ ነጋሽ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተፈራ ፡ ነጋሽ
(Tefera Negash)

Tefera Negash 1.jpg


(1)

አልመለስም
(Alemelesem)

ዓ.ም. (Year): 2011
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተፈራ ፡ ነጋሽ ፡ አልበሞች
(Albums by Tefera Negash)

አዝ፦ በጐርፍ ፡ በነፋስ ፡ አይወሰድም ፡ ቤቴ
አስተማማኝ ፡ አለት ፡ ቃል ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፪x)

ቃል ፡ ነው ፡ መሠረቴ ፡ ቃል ፡ ነው (፬x)

በእርሱ ፡ የታመነ ፡ ቤቱ ፡ አለት ፡ ላይ ፡ ነው
ነፋሱም ፡ አይገፋው ፡ ወጀብ ፡ አይጥለው
ሕያው ፡ የሚሰራ ፡ ቃል ፡ አለኝና
አሻግሬ ፡ የማየው ፡ ድል ፡ አለ ፡ ገና

አነስተኛ ፡ ቢመስልም ፡ ጅማሬዬ
እጅግ ፡ ታላቅ ፡ ይሆናል ፡ ፍጻሜዬ
ትምክህቴ ፡ ከላይ ፡ ነው ፡ ከአርያም
ነገ ፡ ምን ፡ ይሆናል ፡ ብዬ ፡ አልሰጋም

ሳልናወጥ ፡ መቆሜ ፡ ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ደንቆታል
የአምላኬ ፡ ሰላም ፡ ወርዶ ፡ ልቤን ፡ ሙሉ ፡ አድርጐታል
አወዳደቁ ፡ ታላቅ ፡ መጨረሻው ፡ የከፋ
እንደ ፡ አሸዋ ፡ ላይ ፡ ቤት ፡ አይደለም ፡ የኔ ፡ ተስፋ

መኖሪያዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም (፬x)

ፀጋ ፡ ወርዶልኛል ፡ ከአርያም ፡ በፍፁም ፡ ወደኋላ ፡ አልልም
ለሰማዩ ፡ ርስቴ ፡ እጋደላለሁ ፡ በአምላኬ ፡ ታምኜ ፡ እወርሰዋለሁ
የሚያስጨንቀኝን ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ ጥዬ ፡ በወደደኝ ፡ ጌታ ፡ ተደላልድዬ
እተማመናለሁ ፡ በቃልኪዳኑ ፡ አይርድም ፡ ጉልበቴ ፡ ቢከፋም ፡ ቀኑ

አዝ፦ በጐርፍ ፡ በነፋስ ፡ አይወሰድም ፡ ቤቴ
አስተማማኝ ፡ አለት ፡ ቃል ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፪x)

ቃል ፡ ነው ፡ መሠረቴ ፡ ቃል ፡ ነው (፬x)

ከመቅደሱ ፡ የወጣ ፡ የወረደ ፡ ከሰማይ
እርሱ ፡ ነው ፡ መመኪያዬ ፡ የማዕዘኑ ፡ ድንጋይ
በእምነት ፡ የታነጸ ፡ ጥብቅ ፡ ነው ፡ መሠረቴ
በሽብር ፡ አይናጋ ፡ አይናወጥም ፡ ቤቴ

መኖሪያዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም (፬x)