መሸሸጊያ (Mesheshegiya) - ተፈራ ፡ ነጋሽ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተፈራ ፡ ነጋሽ
(Tefera Negash)

Tefera Negash 1.jpg


(1)

አልመለስም
(Alemelesem)

ዓ.ም. (Year): 2011
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተፈራ ፡ ነጋሽ ፡ አልበሞች
(Albums by Tefera Negash)

እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ነው ፡ መልካም ፡ ነው
በመከራ ፡ ቀን ፡ መሸሸጊያ ፡ ነው
አምላካችን ፡ መልካም ፡ ነው ፡ መልካም ፡ ነው
በመከራ ፡ ቀን ፡ መሸሸጊያ ፡ ነው

በመልካም ፡ መንገድ ፡ የሚመራ ፡ ያመኑትን ፡ የማያሳፍር
ለተጨነቁት ፡ ፈጥኖ ፡ ደራሽ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ቃሉን ፡ የሚያከብር
ዝናብ ፡ ደመና ፡ በሌለበት ፡ ምድረ ፡ በዳውን ፡ አለምልሞ
በፍፁም ፡ በረከት ፡ ያኖራል ፡ በድንቅ ፡ ስራው ፡ አስገርሞ

አዝ፦ መልካም ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ነው (መልካም) (፬x)

መሸሸጊያ ፡ ነው ፡ መሸሸጊያ ፡ መሸሸጊያ (፬x)
እያየሁኝ ፡ ሲረዳኝ ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁኝ
እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ እቀኛለሁ
እያየሁኝ ፡ ሲረዳኝ ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁኝ
እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ እቀኛለሁ

አዝ፦ መልካም ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
መልካም ፡ ነው (መልካም ፡ ነው) (፬x)

ሁን ፡ ያለው ፡ ሁሉ ፡ የሚሆንለት ፡ ሥሙ ፡ ገናና ፡ የከበረ
ሃሳቡ ፡ የማይከለከል ፡ ያለ ፡ የሚኖር ፡ የነበረ
አዋጅ ፡ ገልብጦ ፡ የሚያከብር ፡ ከእቶን ፡ እሳት ፡ የሚያድን
መልካም ፡ እረኛ ፡ የት ፡ ይገኛል ፡ እንደ ፡ ክርስቶስ ፡ የሚሆን

አዝ፦ መልካም ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
መልካም ፡ ነው (መልካም ፡ ነው) (፬x)

እያየሁኝ ፡ ሲረዳኝ ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁኝ
እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ እቀኛለሁ (፪x)