ባለውለታዬ (ምሥጋና) - ተፈራ ፡ ነጋሽ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተፈራ ፡ ነጋሽ
(Tefera Negash)

Tefera Negash 1.jpg


(1)

አልመለስም
(Alemelesem)

ዓ.ም. (Year): 2011
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተፈራ ፡ ነጋሽ ፡ አልበሞች
(Albums by Tefera Negash)

አዝ፦ ስራዬን ፡ ሰርተህልኛል ፡ እዳዬን ፡ ከፍለህልኛል
መንገዴ ፡ ተቃንቶልኛል ፡ አንተን ፡ ማየት ፡ ሆኖልኛል
በዘለዓለም ፡ ፍቅርህ ፡ ወድደኸኛልና
ምሥጋና ፡ አይጠፋም ፡ ከአፌ ፡ ምሥጋና (፬x)

አንተ ፡ የደስታዬ ፡ ምንጭ ፡ ውዴ ፡ የሰላሜ ፡ ንጉሥ
ከትቢያ ፡ ላይ ፡ ያነሳኸኝ ፡ ክበር ፡ ተመስገን ፡ ኢየሱስ
ባለፍኩበት ፡ መንገድ ፡ ሁሉ ፡ አይቻለሁ ፡ ማዳንህን
ሳልታክት ፡ አወራዋለሁ ፡ አምላኬ ፡ ሕያው ፡ ስራህን

በተከበበ ፡ ከተማ ፡ ምህረትህ ፡ በዝቶልኝ
በድል ፡ መንገድ ፡ እየመራህ ፡ ከጠላቴ ፡ አስጥለኀኝ
የሞተውን ፡ ማንነቴን ፡ ሕይወት ፡ ዘርተህበታል
ከብረህልኛል ፡ በቤቴ ፡ በረከትህ ፡ በርክቷል (፪x)

አዝ፦ ስራዬን ፡ ሰርተህልኛል ፡ እዳዬን ፡ ከፍለህልኛል
መንገዴ ፡ ተቃንቶልኛል ፡ አንተን ፡ ማየት ፡ ሆኖልኛል
በዘለዓለም ፡ ፍቅርህ ፡ ወድደኸኛልና
ምሥጋና ፡ አይጠፋም ፡ ከአፌ ፡ ምሥጋና (፬x)

የዓለም ፡ እንከን ፡ የሞላበት ፡ ውል ፡ አልባ ፡ ሆኖ ፡ መንገዴ
አንተን ፡ እንዳላይ ፡ ከልሎኝ ፡ አጉል ፡ ወግና ፡ ልማዴ
ምንም ፡ በጐነት ፡ ሳይኖረኝ ፡ እንዲያው ፡ ምህረት ፡ አግኝቼ
የደምህ ፡ ፍሬ ፡ ሆኛለሁ ፡ ከኀጢአት ፡ ባሕር ፡ ወጥቼ

ምሥጋናዬን ፡ ልሰዋልህ ፡ ክበርልኝ ፡ ዘለዓለም
በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ለእኔ ፡ እንዳንተ ፡ መልካም ፡ የለም
እፎይ ፡ ብያለሁ ፡ አርፌ ፡ ሆነኸኛል ፡ ሰላሜ
ተባረክልኝ ፡ ልበልህ ፡ ደግሜ ፡ ደጋግሜ (፪x)

አዝ፦ በዘለዓለም ፡ ፍቅርህ ፡ ወድደኸኛልና
ምሥጋና ፡ አይጠፋም ፡ ከአፌ ፡ ምሥጋና (፬x)

የሞተውን ፡ ማንነት ፡ ሕይወትን ፡ ዘርተህበት
ጽድቅህን ፡ ሰጥተኸኝ ፡ ለእኔ ፡ ነፃ ፡ አረግከኝ ፡ ከኩነኔ

አዝ፦ በዘለዓለም ፡ ፍቅርህ ፡ ወድደኸኛልና
ምሥጋና ፡ አይጠፋም ፡ ከአፌ ፡ ምሥጋና (፬x)