ሃገር ፡ አለኝ (Hager Alegn) - ተፈራ ፡ ነጋሽ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተፈራ ፡ ነጋሽ
(Tefera Negash)

Tefera Negash 1.jpg

(1)

አልመለስም
(Alemelesem)

ዓ.ም. (Year): 2011
ቁጥር (Track):

(7)

ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተፈራ ፡ ነጋሽ ፡ አልበሞች
(Albums by Tefera Negash)

በጐህ ፡ ብርሃን ፡ ወደ ፡ ሆነላት ፡ ከተማ
ላልመለስ ፡ ከልብ ፡ ወስኛለሁ ፡ በዓላማ
እጓዛለሁ ፡ እሄዳለሁ ፡ ጠባቡን ፡ መንገድ ፡ ይዣለሁ
በዘመኑ ፡ መጨረሻ ፡ ከአምላኬ ፡ ጋር ፡ እኖራለሁ

የልጁን ፡ መልክ ፡ እንድመስል ፡ ተወስኖልኛል
ከምድር ፡ ሕይወቴ ፡ ባሻገር ፡ ሰማይ ፡ ክብር ፡ ይጠብቀኛል
ጊዜው ፡ ሲደርስ ፡ የሚገለጥ ፡ በእውነት ፡ የሚታይ
በክርስቶስ ፡ የወረስኩት ፡ ሃገር ፡ አለኝ ፡ በሰማይ

አዝ፦ ሃገር ፡ አለኝ ፡ በሰማይ ፡ ሃገር ፡ አለኝ (ሃገር ፡ አለኝ)
እግዚአብሔር ፡ ያዘጋጀልኝ ፡ ሃገር ፡ አለኝ (ሃገር ፡ አለኝ)
እርስት ፡ አለኝ ፡ በሰማይ ፡ እርስት ፡ አለኝ (እርስት ፡ አለኝ)
እግዚአብሔር ፡ ያዘጋጀልኝ ፡ ሃገር ፡ አለኝ (ሃገር ፡ አለኝ)

ከከፍታዬ ፡ ላይ ፡ በጭራሽ ፡ አልወርድም
ወደፊት ፡ እያየሁ ፡ ወደኋላ ፡ አልሄድም
ኃይልን ፡ በሚሰጠኝ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ
በክርስቶስ ፡ ፀጋ ፡ በድል ፡ እጓዛለሁ

ኢየሩሳሌም ፡ ኢየሩሳሌም ፡ ኢየሩሳሌም ፡ እገባለሁ (፪x)

ምንም ፡ አስቸጋሪ ፡ ቢሆን ፡ መውደቅ ፡ መነሳቱ
ላይደክም ፡ ላይዝል ፡ ጉልበቴ ፡ ጌታ ፡ አድርጐኛል ፡ ብርቱ
ጉዞው ፡ በድል ፡ ሲጠናቀቅ ፡ ህልሜ ፡ ግብ ፡ ሲመታ
ከበጉ ፡ ጋር ፡ እኖራለሁ ፡ ፍፁም ፡ በሆነ ፡ ደስታ

አዝ፦ ሃገር ፡ አለኝ ፡ በሰማይ ፡ ሃገር ፡ አለኝ (ሃገር ፡ አለኝ)
እግዚአብሔር ፡ ያዘጋጀልኝ ፡ ሃገር ፡ አለኝ (ሃገር ፡ አለኝ)
እርስት ፡ አለኝ ፡ በሰማይ ፡ እርስት ፡ አለኝ (እርስት ፡ አለኝ)
እግዚአብሔር ፡ ያዘጋጀልኝ ፡ ሃገር ፡ አለኝ (ሃገር ፡ አለኝ)

ሃገር ፡ አለኝ ፡ በሰማይ ፡ ሃገር ፡ አለኝ
እግዚአብሔር ፡ ያዘጋጀልኝ ፡ ሃገር ፡ አለኝ