ገለል ፡ ይላል (Gelel Yelal) - ተፈራ ፡ ነጋሽ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ተፈራ ፡ ነጋሽ
(Tefera Negash)

Tefera Negash 1.jpg


(1)

አልመለስም
(Alemelesem)

ዓ.ም. (Year): 2011
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተፈራ ፡ ነጋሽ ፡ አልበሞች
(Albums by Tefera Negash)

እኔ ፡ ግን ፡ ሁሉን ፡ ለሚችለው ፡ ለርሱ ፡ ተለይቻለሁ
በተቀደሰው ፡ ተራራዬ ፡ ንጉሤን ፡ ሾሜዋለሁ (፪x)

አመልከዋለሁ ፡ በቤቴ ፡ አከብረዋለሁ
አነግሰዋለሁ ፡ በልቤ ፡ እቀድሰዋለሁ (፪x)

ከተነገረለት ፡ ከተባለው ፡ በላይ
ትልቅ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ በምድር ፡ በሰማይ
እሰግድለታለሁ ፡ ይገባዋል ፡ እሱ
ከፍ ፡ አደርገዋለሁ ፡ በቤተ ፡ መቅደሱ

ኤልሻዳዩን ፡ አምላክ ፡ ሳመልከው ፡ ከልቤ (፪x)
ስሙን ፡ ሳወድሰው ፡ በፍፁም ፡ ሃሳቤ (፪x)
ምን ፡ ይሳነዋል ፡ ጌታ ፡ ታምራት ፡ ይሆናል (፪x)
የሚገዳደረኝም ፡ ጥሎኝ ፡ ገለል ፡ ይላል

አዝ፦ ገለል ፡ ይላል (፫x)
ከፊቴ ፡ ገለል ፡ ይላል (፪x)

ቢመከር ፡ ቢዶለት ፡ ወጥመድ ፡ ቢዘረጋ
የጠላት ፡ ሠራዊት ፡ ሺህ ፡ ሆኖ ፡ ቢንጋጋ
እውነት ፡ እንደ ፡ ጋሻ ፡ ዙሪያዬን ፡ ከብቦኝ
ምልክት ፡ አለብኝ ፡ በየት ፡ ሊያገኘኝ

በነፍሥም ፡ እንኳን ፡ ቢሆንም ፡ እወራረዳለሁ (፪x)
ከሚነድም ፡ እሳት ፡ ያድናል ፡ አምናለሁ (፪x)
የቃልኪዳን ፡ ልጅ ፡ ነኝ ፡ ይሄው ፡ ነው ፡ ትምክህቴ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ትምክህቴ
ጭንገፋና ፡ እርግማን ፡ አይገቡም ፡ በቤቴ (፪x)

የጌታን ፡ ሥም ፡ ስጠራ ፡ ችግር ፡ ቢሆን ፡ መከራ
ኢየሱስን ፡ ስጠራ ፡ ሸለቆ ፡ ቢሆን ፡ ተራራ
የስልጣኑን ፡ ጉልበት ፡ መቼ ፡ ይቋቋማል

አዝ፦ ገለል ፡ ይላል ፡ ከፊቴ ፡ ገለል ፡ ይላል (፫x)