ቸር ፡ ነውና (Cher Newena) - ተፈራ ፡ ነጋሽ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተፈራ ፡ ነጋሽ
(Tefera Negash)

Tefera Negash 1.jpg


(1)

አልመለስም
(Alemelesem)

ዓ.ም. (Year): 2011
ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተፈራ ፡ ነጋሽ ፡ አልበሞች
(Albums by Tefera Negash)

አዝ፦ ቸር ፡ ነውና ፡ ምህረቱ ፡ የለው ፡ ወደር
ክብር ፡ ይሁንለት ፡ በሰማይ ፡ በምድር
እልል ፡ በሉ ፡ ዘምሩለት ፡ በበገና
አምልኮ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይገባዋልና
ይገባዋል (፰x)

ሰማይና ፡ ምድርን ፡ በቃሉ ፡ ያጸና
ሁሉን ፡ የፈጠረ ፡ ኃያል ፡ ባለዝና
በእውነት ፡ እንደ ፡ ቃሉ ፡ ፍፁም ፡ የታመነ
አልፋና ፡ ኦሜጋ ፡ ኤልሻዳይ ፡ የሆነ
ዘለዓለማዊ ፡ አምላክ ፡ ሁሉ ፡ ይቻለዋል
አምልኮና ፡ ስግደት ፡ ክብር ፡ ይገባዋል

ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ (፬x)

አዝ፦ ቸር ፡ ነውና ፡ ምህረቱ ፡ የለው ፡ ወደር
ክብር ፡ ይሁንለት ፡ በሰማይ ፡ በምድር
እልል ፡ በሉ ፡ ዘምሩለት ፡ በበገና
አምልኮ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይገባዋልና
ይገባዋል (፰x)

የሞት ፡ አዋጅ ፡ ሽሮ ፡ ሕይወትን ፡ የሚሰጥ
መራራውን ፡ ሃዘን ፡ በሳቅ ፡ የሚለውጥ
አጥፊውን ፡ አጥፍቶ ፡ ምስኪኑን ፡ ያከብራል
ሃሳቡ ፡ እንደዋዛ ፡ መቼ ፡ ይከለከላል
ማደሪያው ፡ ይባረክ ፡ ክብር ፡ ይሁንለት
የፍጥረታት ፡ ጌታ ፡ የሕያዋን ፡ አባት

ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ (፬x)