ቤዛህ (Biezah) - ተፈራ ፡ ነጋሽ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተፈራ ፡ ነጋሽ
(Tefera Negash)

Tefera Negash 1.jpg


(1)

አልመለስም
(Alemelesem)

ዓ.ም. (Year): 2011
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተፈራ ፡ ነጋሽ ፡ አልበሞች
(Albums by Tefera Negash)

ተኩላው ፡ ለምድ ፡ ለብሶ ፡ እውነትን ፡ አለባብሶ
ሲዖል ፡ እንዳይከትህ ፡ ንቃ ፡ በል ፡ ወገኔ ፡ አስተውል
አምልጥ ፡ ከጠላትህ ፡ ወዳጅ ፡ መስሎ ፡ ሳይገድልህ
በጉብዝናህ ፡ ወራት ፡ አምላክህን ፡ አስብ ፡ ፈጣሪህን

መዳን ፡ በሌላ ፡ የለም ፡ አትታለል ፡ ወገኔ
እዳህን ፡ የከፈለው ፡ ይልሃል ፡ ና ፡ ወደኔ
ከሞት ፡ መንገድ ፡ ተመለስ ፡ ኋላ ፡ ሳያጠፋህ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ከሲዖል ፡ ከሞት ፡ የሚያድንህ

ሃብትህ ፡ ሞልቶ ፡ ቢትረፈረፍ ፡ ለዓለም ፡ ሁሉ ፡ ቢበቃ
ዝናህ ፡ ከአጥናፍ ፡ አጥናፍ ፡ ቢደርስ ፡ ለጊዜውም ፡ ቢያስመካህ
ስልጣን ፡ ዕውቀትም ፡ ቢኖርህ ፡ የነገሥታት ፡ ዘር ፡ ብትሆን
ዋስትናህ ፡ ግን ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ለነፍስህ ፡ ቤዛ ፡ የሚሆን

አዝ፦ ቤዛህ ፡ ቤዛህ ፡ ቤዛህ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፬x)

የሚደግፍህ ፡ የሌለ ፡ ብትሆንም ፡ ችግረኛ
ተስፋ ፡ ቆርጠህ ፡ የምትባዝን ፡ ያለምንም ፡ መጽናኛ
ለጥያቄዎችህ ፡ ሁሉ ፡ መልስ ፡ የሚሆን ፡ በእውነት
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ በደጅህ ፡ ነው ፡ በርህን ፡ ክፈትለት

አስቀድመህ ፡ ከሁሉ ፡ አምላክህን ፡ ውደድ
እንዲያሳይህ ፡ በጸጋው ፡ የሕይወትን ፡ መንገድ
እሺ ፡ ብትል ፡ ለጌታ ፡ ብትታዘዝ ፡ ለቃሉ
በበረከት ፡ ይሞላል ፡ የጐደለህ ፡ በሙሉ