Tefera Negash/Alemelesem/Abat Aggnchalehu

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ጠላቴ ፡ ያሻውን ፡ ቢያወራ ፡ አልሰማም ፡ እንኳንስ ፡ ልፈራ አምላኬ ፡ ጥላ ፡ ስር ፡ አድራለሁ ፡ አስተማማኝ ፡ ጋሻ ፡ አግኝቻለሁ ዲያቢሎስ ፡ ቢፎክር ፡ ቢያወራ ፡ አልሰማም ፡ እንኳንስ ፡ ልፈራ አምላኬ ፡ ጥላ ፡ ስር ፡ አድራለሁ ፡ የሚያኮራ ፡ አባት ፡ አግኝቻለሁ

አዝ፦ አግኝቻለሁ ፡ አባት ፡ አግኝቻለሁ (፬x)

ደሙ ፡ በጉ ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ ስላለ ፡ ጥፋት ፡ መቼም ፡ አያገኘኝ እንደ ፡ ዐይኑ ፡ ብሌን ፡ ይጠብቀኛል ፡ እግዚአብሔር ፡ መቼም ፡ አይተወኝ ያ ፡ የጨለማ ፡ ዘመን ፡ አለፈ ፡ አበቃ ፡ ብርሃን ፡ በራ አሻገረኝ ፡ በበረታች ፡ ክንዱ ፡ ነፃ ፡ ወጣሁ ፡ በአምላክ ፡ ስራ

ፈርዖን ፡ ከኋላ ፡ ቀይ ፡ ባሕር ፡ ከፊቴ
ከብቦኝ ፡ ቢደነፋ ፡ ቢፎክር ፡ ጠላቴ
እግዚአብሔር ፡ ሲነሳ ፡ ጠላቶቼ ፡ ሁሉ ፡ በሰባት ፡ መንገድ ፡ ይበታተናሉ
ኃያሉ ፡ ሲነሳ ፡ የከበቡኝ ፡ ሁሉ ፡ በሰባት ፡ መንገድ ፡ ይበታተናሉ

ምድሩን ፡ ማዕበሉን ፡ አልፈራ ፡ እግዚአብሔር ፡ በኃይሉ ፡ አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ በአምላኬ ፡ እተማመናለሁ ፡ ጠላቴ ፡ ይሰጥማል ፡ እኔ ፡ እሻገራለሁ

አዝ፦ አግኝቻለሁ ፡ አባት ፡ አግኝቻለሁ (፬x)

ማዕበል ፡ ወጀቡ ፡ ቢነሳ ፡ ተራራው ፡ ቢገተር ፡ ከፊቴ ሁሉም ፡ ትክክል ፡ ይሆናል ፡ ትዕዛዝ ፡ ሲወጣ ፡ ከአባቴ መድኃኒቴ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ አልፈራም ፡ እተማመናለሁ እባቡን ፡ እና ፡ ዘንዶውን ፡ እረጋግጬው ፡ አልፋለሁ

ሰይጣን ፡ ተማምሎ ፡ ሊያጠፋኝ ፡ ቢነሳ ሊውጠኝ ፡ ቢጐመጅ ፡ ዙሪያዬን ፡ ቢያገሳ ልቤ ፡ አይደነግጥም ፡ በከንቱ ፡ ፉከራ እግዚአብሔር ፡ ጋሻዬ ፡ አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ልቤ ፡ አይደነግጥም ፡ በከንቱ ፡ ፉከራ እግዚአብሔር ፡ አባቴ ፡ አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ

ከእኔ ፡ ጋራ ፡ አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
ከእኔ ፡ ጋራ ፡ አምላክ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
ከእኔ ፡ ጋራ ፡ አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ጌታ ፡ ከኔ ፡ ጋራ

ፈርዖን ፡ ከኋላ ፡ ቀይ ፡ ባሕር ፡ ከፊቴ ከብቦኝ ፡ ቢደነፋ ፡ ቢፎክር ፡ ጠላቴ እግዚአብሔር ፡ ሲነሳ ፡ ጠላቶቼ ፡ ሁሉ ፡ በሰባት ፡ መንገድ ፡ ይበታተናሉ ኃያሉ ፡ ሲነሳ ፡ የከበቡኝ ፡ ሁሉ ፡ በሰባት ፡ መንገድ ፡ ይበታተናሉ

ወጀቡን ፡ ማዕበሉን ፡ አልፈራ ፡ እግዚአብሔር ፡ በኃይሉ ፡ አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ በአምላኬ ፡ እተማመናለሁ ፡ ጠላቴ ፡ ይሰጥማል ፡ እኔ ፡ እሻገራለሁ

አዝ፦ አግኝቻለሁ ፡ አባት ፡ አግኝቻለሁ (፰x)

</poem> }}