ወንድም ጋሼ (Yemtsasalgn Yemtwedegn) - ታምራት ፡ ኃይሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ታምራት ፡ ኃይሌ
(Tamrat Haile)

Lyrics.jpg


(4)

የምትሳሳልኝ ፡ የምትወደኝ
(4)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፸ ፬ (1982)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 5:28
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ኃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

አዝ፥ የምትሳሳልኝ የምትወደኝ
ከማንም ይልቅ የምትቀርበኝ
የምትጠብቀኝ ጠዋት ማታ
ጠላቴን በስውር የምትመታ
የምትበቀልልኝ ደም መላሼ
ስምህ ብሩክ ይሁን ወንድም ጋሼ

1.እናት ሆነህ ጡትክን ያጠባኸኝ
አባት ሆነህ ቀጥተህ ያሳደከኝ
እነደ ታላቅ ወንድም የምትመክረኝ
እንደ እህት ደብቀህ ያጎረስከኝ
         ደግሞም ወዳጄ ነህ ሚስጥረኛዬ
         የትም የማትለየኝ ጓደኛዬ
         የጠላቴ ጠላት ደም መላሼ
         ስምህ ብሩክ ይሁን ወንድም ጋሼ
አዝ
2.ቁስልህን ስወጋ ሳሳዝንህ
በትቢት እየሄድኩ ሳስቸግርህ
ፊትህ ሲከብድብኝ ስትቆጣኝ
ጅራፍ ስታነሳ ልትቀጣኝ
        ወዲያዉ ደግሞ ተንበርክኬ አልቅሼ
        ጌታ ማረኝ ስልህ ተመልሼ
        በዚያው ክትት አይልም ጨርሶ
        እጅህ ይዘረጋል ተመልሶ
አዝ
3.አንተ እያለህ መቼ ይበርደኛል
ፀጋህን ስደርብ ይሞቀኛል
ሲርበኝ እግርህ ስር እወድቃለሁ
ፊትህን ሳይ ወዲያው እጠግባለሁ
        አዝኜም በፊትህ እደፋለሁ
        ቀና ስል በደስታ እሞላለሁ
        ምን ልመልስልህ በዚህ ፈንታ
        ስምህ ብሩክ ይሁን የኔ ጌታ
አዝ
4.እጄ ምንም ሳይኖር ደሃ ሳለሁ
በድህነቴ አንተን አግኝቻለሁ
አላጥላላኸኝም ወደኸኛል
ከነ ግሳን ግሴ አቅፈኸኛል
        አሁንም በፀጋህ እቆማለሁ
        እስካኖርከኝ ድረስ እኖራለሁ
        የሚቆጨው ካለ ይረር እንጂ
        እኔ እንደው አልወጣም ካንተ ደጅ
አዝ
5.አባት ቢሉህ እናት ቢሉህ ወንድም
  ቢሉህ እህት ቢሉህ ወዳጅ ባለንጀራ
  ጌታ ሆይ ምን አለ የማትሞላው ስፍራ
         የድሃደጎች አባት ነክ አዎ
         ለመበለቶችም ዳኛ አዎ
         ለታላላቆች ተቆጪ አዎ
         ለታናናሾች እረኛ አዎ
         የተራቡትን መጋቢ አዎ
         የተገፉትን ሰብሳቢ አዎ
         ሁሉም አንተው ነህ እራስህ አዎ
         ክብር ምስጋና ይድረስህ አዎ
አዝ