ማንን ፡ እንደጣለ ፡ ይጥልሃል (Manen Endetale Yetelehal) - ታምራት ፡ ኃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ማንን ፡ እንደጣለ ፡ ይጥልሀል
ማንን ፡ እንደተወ ፡ ይተውሀል
ጌታ ፡ አንተን ፡ እጅግ ፡ ይወድሀል

ሁሉን ፡ ያደርግ ፡ ዘንድ ፡ ቻይ ፡ ነውና ፡ አምላኬ
እጠብቀዋለው ፡ ፊቱ ፡ ተንበርክኬ ፡
አዋጅን ፡ በአዋጅ ፡ ሲሽር ፡ ሰምቻለው
እሳትን ፡ በእሳት ፡ ሲያጠፋ ፡ አይቻለው

አዝ፦ ማንን ፡ እንደጣለ ፡ ይጥልሀል
ማንን ፡ እንደተወ ፡ ይተውሀል
ጌታ ፡ አንተን ፡ እጅግ ፡ ይወድሀል

የቆሸሸን ፡ ታሪክ ፡ ከማህደር ፡ ያወጣል
ልብን ፡ ብቻ ፡ አይደለም ፡ ስምን ፡ ይለውጣል
በሰው ፡ የተናቁ ፡ መንገድ ፡ የተጣሉ
ብዙዎች ፡ ናቸው ፡ በርሱ ፡ አንቱ ፡ የተባሉ

አዝ፦ ማንን ፡ እንደጣለ ፡ ይጥልሀል
ማንን ፡ እንደተወ ፡ ይተውሀል
ጌታ ፡ አንተን ፡ እጅግ ፡ ይወድሀል

ለሰይጣን ፡ ሹክሹክታ ፡ ጆሮህን ፡ አትክፈት
ጌታ ፡ ያነሳሀል ፡ ዛሬ ፡ ካለህበት
ሁሉም ፡ ነገር ፡ አልፎ ፡ ታሪክ ፡ ታወራለህ
ስለክብሩ ፡ ቆመህ ፡ ትመሰክራለህ

አዝ፦ ማንን ፡ እንደጣለ ፡ ይጥልሀል
ማንን ፡ እንደተወ ፡ ይተውሀል
ጌታ ፡ አንተን ፡ እጅግ ፡ ይወድሀል

እንደ ፡ አውራ ፡ ጎዳና ፡ ሆነህ ፡ መራገጫ
ሁሉም ፡ ለምኞቱ ፡ አርጐህ ፡ መወጣጫ
እንደወደክ ፡ አትቀር ፡ እንደተረሳህ
ጨው ፡ ነው ፡ የምትሆነው ፡ ጌታ ፡ ሲያነሳህ