From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ ጌታቸው ፡ በመጣ ፡ ጊዜ ፡ ሲተጉ ፡ የሚያገኛቸው
እነዚያ ፡ ባሮች ፡ ብጹኁን ፡ ናቸው (፪x)
አስቀምጦ ፡ ያገለግላቸዋል ፡ በማዕዱ
እኔንም ፡ አርገኝ ፡ ከእነርሱ ፡ እንደ ፡ አንዱ
ቀጠሮ ፡ አፍራሽ ፡ የጊዜ ፡ ሌባ ፡ መምሸቱን ፡ አውቆ ፡ ቤቱ ፡ ማይገባ
ከዘመን ፡ ኋላ ፡ ኋላ ፡ ተጎታች ፡ የሁሉም ፡ ጭራ ፡ ከሁሉም ፡ በታች
ከቶ ፡ የማይገባኝ ፡ የህይወት ፡ ነገር ፡ እንዳልሆንብህ ፡ እንዳትቸገር
እግሬ ፡ መራመድ ፡ እንዳያቅተው ፡ የሩቁን ፡ እንዳይ ፡ አይኔን ፡ ክፈተው
አዝ፦ ጌታቸው ፡ በመጣ ፡ ጊዜ ፡ ሲተጉ ፡ የሚያገኛቸው
እነዚያ ፡ ባሮች ፡ ብጹኁን ፡ ናቸው (፪x)
አስቀምጦ ፡ ያገለግላቸዋል ፡ በማዕዱ
እኔንም ፡ አርገኝ ፡ ከእነርሱ ፡ እንደ ፡ አንዱ
ዓለም ፡ ስትከፋ ፡ ዘመን ፡ ሲጨልም ፡ ምርምር ፡ በዝቶ ፡ እምነት ፡ ሲደክም
ፈጣሪን ፡ መፍራት ፡ ከምድር ፡ ሲጠፋ ፡ ፍጥረት ፡ ሲደገፍ ፡ በራሱ ፡ ተስፋ
ቆይ ፡ ይደረሳል ፡ ማለት ፡ ይበቃል ፡ ነገን ፡ መኖሬን ፡ እግዚአብሄር ፡ ያውቃል
ይልቅ ፡ ልነሳ ፡ ልክፈተው ፡ ደጁን ፡ መለከት ፡ ልንፋ ፡ ልንገር ፡ አዋጁን
አዝ፦ ጌታቸው ፡ በመጣ ፡ ጊዜ ፡ ሲተጉ ፡ የሚያገኛቸው
እነዚያ ፡ ባሮች ፡ ብጹኁን ፡ ናቸው (፪x)
አስቀምጦ ፡ ያገለግላቸዋል ፡ በማዕዱ
እኔንም ፡ አርገኝ ፡ ከእነርሱ ፡ እንደ ፡ አንዱ
የመምጫውን ፡ ቀን ፡ ከቶ ፡ ማን ፡ ያውቃል ፡ ጠብቁኝ ፡ ብሎ ፡ ያስጠነቅቃል
የድል ፡ መለከት ፡ ሲነፋ ፡ ከላይ ፡ አንዷ ፡ በወፍጮ ፡ ሌላው ፡ በእርሻው ፡ ላይ
ምጥ ፡ እርጉዝን ፡ ሴት ፡ እንደሚይዛት ፡ ድንገት ፡ ይሆናል ፡ የጌታ ፡ መምጣት
በውጭ ፡ ጨለማ ፡ መጣል ፡ ይመጣል ፡ በተጠንቀቅ ፡ ግን ፡ መቆም ፡ ያዋጣል
አዝ፦ ጌታቸው ፡ በመጣ ፡ ጊዜ ፡ ሲተጉ ፡ የሚያገኛቸው
እነዚያ ፡ ባሮች ፡ ብጹኁን ፡ ናቸው (፪x)
አስቀምጦ ፡ ያገለግላቸዋል ፡ በማዕዱ
እኔንም ፡ አርገኝ ፡ ከእነርሱ ፡ እንደ ፡ አንዱ
የማጽናኛ ፡ ቃል ፡ ለደከሙቱ ፡ የጥሪ ፡ ደወል ፡ ውጪ ፡ ላሉቱ
በህይወት ፡ ማእበል ፡ ለሚንገላቱ ፡ የጸሎት ፡ ድጋፍ ፡ እንዲበረቱ
አልነጋ ፡ ላለው ፡ ለጨለመበት ፡ መቆም ፡ እንድችል ፡ በፈረሰበት
ባርከኝ ፡ በብዙ ፡ አታሳንሰኝ ፡ እየቆራረጥክ ፡ ለብዙ ፡ አድርሰኝ
|