From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
በሳር ፡ ብንሰራ ፡ ባገዳ
ተቃጥሎብን ፡ እንዳንጎዳ
የሚያነጥር ፡ እሳት ፡ ሲመጣ
ማነው ፡ ተፈትኖ ፡ ሚወጣ
አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ ምለምንህ ፡ (እለምንሀለው) ፡ አንድ ፡ ነገር
የኖርኩትን ፡ ኑሮ ፡ እንድናገር
የተናገርኩትን ፡ እንድኖር (፪x)
እርዳኝ ፡ በዚህ ፡ ዘመን
በጨለማ ፡ የተሰወረ ፡
በማስመሰል ፡ ኑሮ ፡ የኖረ
ወደ ፡ ብርሀን ፡ ታወጣለህ
ለሁሉም ፡ እንደስራው ፡ ትከፍላለህ
አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ ምለምንህ ፡ (እለምንሀለው) ፡ አንድ ፡ ነገር
የኖርኩትን ፡ ኑሮ ፡ እንድናገር
የተናገርኩትን ፡ እንድኖር (፪x)
እርዳኝ ፡ በዚህ ፡ ዘመን
አንዳንዱ ፡ ለደሞዝ ፡ ይሰብካል
ሌላኛው ፡ ለጥቅም ፡ ያመልካል
ታዲያ ፡ ማነው ፡ አንተን ፡ ፈላጊ
የተናገረውን ፡ አድራጊ
አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ ምለምንህ ፡ (እለምንሀለው) ፡ አንድ ፡ ነገር
የኖርኩትን ፡ ኑሮ ፡ እንድናገር
የተናገርኩትን ፡ እንድኖር (፪x)
እርዳኝ ፡ በዚህ ፡ ዘመን
ባፌ ፡ ብዙ ፡ ፍቅርን ፡ ስገልጥ
ወንድሜን ፡ በነገር ፡ ስረግጥ
ቃል ፡ አባይ ፡ ሆኜ ፡ እንዳልገኝ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ከሀሰት ፡ ጠብቀኝ
አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ ምለምንህ ፡ (እለምንሀለው) ፡ አንድ ፡ ነገር
የኖርኩትን ፡ ኑሮ ፡ እንድናገር
የተናገርኩትን ፡ እንድኖር (፪x)
እርዳኝ ፡ በዚህ ፡ ዘመን
በጓዳም ፡ ይሁን ፡ በጎዳና
ነውር ፡ የሌለባት ፡ ህሊና
በእግዚአብሄርና ፡ በሰው ፡ ፊት
እንድራመድ ፡ እርዳኝ ፡ በእውነት
|