From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ ዲያቢሎስ ፡ ምነው ፡ ቸኮለ ፡ ሊውጠን ፡ እየከጀለ
መሰለኝ ፡ ቀኑ ፡ ሊደርስ ፡ የሰይጣን ፡ መንግስት ፡ ሊፈርስ
በእርግጥ ፡ ቀኑ ፡ ደርሶ ፡ ነው ፡ የሚይዘው ፡ ግራ ፡ ገብቶት ፡ ነው (፫x)
የገባው ፡ ደረቱን ፡ ነፍቶ ፡ ነጋሪት ፡ ከበሮ ፡ መቶ
ሲወጣ ፡ በጣር ፡ ተይዞ ፡ በጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ስም ፡ ታዞ ፡
አይተናል ፡ ዛሬም ፡ ይሆናል ፡ የኢየሱስ ፡ ስሙ ፡ ያድናል
አዝ፦ ዲያቢሎስ ፡ ምነው ፡ ቸኮለ ፡ ሊውጠን ፡ እየከጀለ
መሰለኝ ፡ ቀኑ ፡ ሊደርስ ፡ የሰይጣን ፡ መንግስት ፡ ሊፈርስ
በእርግጥ ፡ ቀኑ ፡ ደርሶ ፡ ነው ፡ የሚይዘው ፡ ግራ ፡ ገብቶት ፡ ነው (፫x)
ሌባ ፡ ነው ፡ ነፍስን ፡ ይሰርቃል ፡ ከህይወት ፡ መንገድ ፡ ያርቃል
አይገባም ፡ በዋናው ፡ በር ፡ ይያዛል ፡ መስኮት ፡ ሲሰብር
ሲሸፍት ፡ እንደ ፡ ልማዱ ፡ ደቆሰው ፡ ኢየሱስ ፡ በክንዱ
አዝ፦ ዲያቢሎስ ፡ ምነው ፡ ቸኮለ ፡ ሊውጠን ፡ እየከጀለ
መሰለኝ ፡ ቀኑ ፡ ሊደርስ ፡ የሰይጣን ፡ መንግስት ፡ ሊፈርስ
በእርግጥ ፡ ቀኑ ፡ ደርሶ ፡ ነው ፡ የሚይዘው ፡ ግራ ፡ ገብቶት ፡ ነው (፫x)
አድራሻው ፡ አመድ ፡ አተላ ፡ እንደ ፡ ከብት ፡ አሳር ፡ ሲያበላ
የለውም ፡ ክብር ፡ ማእረግ ፡ አያውቅም ፡ ሰው ፡ ማሳደግ
ኢየሱስ ፡ አዳነን ፡ ከእጁ ፡ ሆ ፡ በሉ ፡ ስሙን ፡ አውጁ
አዝ፦ ዲያቢሎስ ፡ ምነው ፡ ቸኮለ ፡ ሊውጠን ፡ እየከጀለ
መሰለኝ ፡ ቀኑ ፡ ሊደርስ ፡ የሰይጣን ፡ መንግስት ፡ ሊፈርስ
በእርግጥ ፡ ቀኑ ፡ ደርሶ ፡ ነው ፡ የሚይዘው ፡ ግራ ፡ ገብቶት ፡ ነው (፫x)
ለመስቀል ፡ እንጨት ፡ ሲቆርጥ ፡ መዶሻ ፡ ሚስማር ፡ ሲሰጥ
መቃብር ፡ ድንጋይ ፡ ሲገጥም ፡ ዘብ ፡ ሲያቆም ፡ ማእተም ፡ ሲያትም
ፈርቶ ፡ ነው ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ አበሳ ፡ አልቀረም ፡ ኢየሱስ ፡ ተነሳ
|