በቀኑ ፡ መጨረሻ (Beqenu Mecheresha) - ታምራት ፡ ኃይሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በየቀኑ ፡ መጨረሻ
ለትውልድ ፡ መፈወሻ ፡ አድርገኝ
አንተን ፡ በመፍራት ፡ አሳድገኝ

ቅጠሌን ፡ አይተው ፡ የተመሰጡ
ፍሬን ፡ ፍለጋ ፡ ቤቴ ፡ ስመጡ
በጣፋጭ ፡ ዜማ ፡ እየጠራሁኣቸው
ያለ ፡ ዉሃ ፡ እንዳሸኛቸው ፡ ።

አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በየቀኑ ፡ መጨረሻ
ለትውልድ ፡ መፈወሻ ፡ አድርገኝ
አንተን ፡ በመፍራት ፡ አሳድገኝ

ስምህ ፡ ተጠርተው ፡ ድንቅን ፡ ስሰራ
የኔ ፡ ገድል ፡ እንዳይወራ
መድረኩም ፡ እንኳ ፡ ብነቃነቅ
አንተን ፡ አክብሬ ፡ ራሴን ፡ ልናቅ።

አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በየቀኑ ፡ መጨረሻ
ለትውልድ ፡ መፈወሻ ፡ አድርገኝ
አንተን ፡ በመፍራት ፡ አሳድገኝ

የውርንጫዋ ፡ የስራ ፡ ድርሻ
ወደ ፡ ኢየሩሳሌም ፡ መድረሻ
ጨርቅ ፡ ብነጠፍ ፡ ሆሳዕና ፡ ብባል
ክብር ፡ ስግደትም ፡ ላንተ ፡ ይገባል።

አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በየቀኑ ፡ መጨረሻ
ለትውልድ ፡ መፈወሻ ፡ አድርገኝ
አንተን ፡ በመፍራት ፡ አሳድገኝ

ባመጽ ፡ ተወልደን ፡ በኃጢኣት ፡ አድጋናል
በጎውን ፡ ነገር ፡ ማን ፡ ያሳየናል
በሚለው ፡ ትውልድ ፡ መካከል ፡ ስገኝ
እውነትን ፡ ገላጭ ፡ ብርሃን ፡ አድርገኝ።

አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በየቀኑ ፡ መጨረሻ
ለትውልድ ፡ መፈወሻ ፡ አድርገኝ
አንተን ፡ በመፍራት ፡ አሳድገኝ

[[Category:አ

ማርኛ]]