From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ ወደ ፡ ሙታን ፡ ትንሳኤ ፡ ለመድረስ ፡ ቢሆንልኝ
በሞቱ ፡ እንድመስለው እመኛለሁ (8x)
የእምነት ፡ አባቶቼን ፡ ሳስባቸው ፡ በደም ፡ የደመቀ ፡ ታሪካቸው
በወህኒ ፡ በስራት ፡ በመከራ ፡ በጉድጓድ ፡ በዋሻ ፡ በተራራ
የተቅበዘበዙ ፡ እሳት ፡ የበላቸው ፡ ለቃልኪዳን ፡ እንጂ ፡ መቼ ፡ ለእንጀራቸው
ምሳሌነታቸው ፡ እንድከተል ፡ አርገኝ ፡ በልክስክስ ፡ ቦታ ፡ ከመሞት ፡ ጠብቀኝ
አዝ፦ ወደ ፡ ሙታን ፡ ትንሳኤ ፡ ለመድረስ ፡ ቢሆንልኝ
በሞቱ ፡ እንድመስለው እመኛለሁ (8x)
ሰው ፡ ሁሉ ፡ ቢክድህ ፡ እኔ ፡ አልክድህ ፡ ካንተ ፡ ይልቅ ፡ እራሴን ፡ አልወድ
ብዬ ፡ ስመጻደቅ ፡ ስቀናጣ ፡ ያቺ ፡ ፈታኝ ፡ ሰዐት ፡ ስትመጣ
ኢየሱስን ፡ አላውቅም ፡ ብዬ ፡ እንዳልራገም ፡ አፌን ፡ ጠብቅልኝ ፡ ዛሬም ፡ ቢሆን ፡ ነገ
መስቀሌን ፡ አግዘኝ ፡ ብለህ ፡ ስትለምነኝ ፡ የዓለምን ፡ እሳት ፡ ከመሞቅ ፡ አድነኝ
አዝ፦ ወደ ፡ ሙታን ፡ ትንሳኤ ፡ ለመድረስ ፡ ቢሆንልኝ
በሞቱ ፡ እንድመስለው : እመኛለሁ (8x)
የአንድ ፡ ሰሞን ፡ ወሬ ፡ ክብር ፡ ዝና ፡ ፡ መስቀል ፡ ያልፈተነው ፡ ጉብዝና
የአንድ ፡ ሰሞን ፡ ሙቀት ፡ ሀሌሉያ ፡ ፡ አይሆንም ፡ መለኪያ ፡ መታወቂያ
ካላለፍኩኝ ፡ በቀር ፡ ያቺን ፡ ቀውጢ ፡ ሰዓት ፡ አንተን ፡ አስከብሬ ፡ በመከራ ፡ እሳት
ፍጻሜዬ ፡ እንዲያምር ፡ ጉዞ ፡ እንዲሰምርልኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ፈሪ ፡ ነኝ ፡ እምነት ፡ ጨምርልኝ
አዝ፦ ወደ ፡ ሙታን ፡ ትንሳኤ ፡ ለመድረስ ፡ ቢሆንልኝ
በሞቱ ፡ እንድመስለው እመኛለሁ (8x)
ደካማው ፡ ስጋዬ ፡ ሲስገበገብ ፡ የዓለም ፡ ነገር ፡ እንደው ፡ አይጠገብ
አንዱን ፡ ስይዝ ፡ ሌላው ፡ እንዳያምረኝ ፡ ኑሮዬ ፡ በቃኝ ፡ ማለትን ፡ አስተምረኝ
ስለ ፡ ስምህ ፡ ክብር ፡ ለመንግስትህ ፡ መስፋት ፡ ሁሉን ፡ መስዋአት ፡ ላድርግ ፡ ለሚጠፉ ፡ ነፍሳት
ገንዘቤ ፡ ገንዘብህ ፡ ቤቴም ፡ የአንተ ፡ ቤት ፡ እንድሞት ፡ አድርገኝ ፡ የጻድቃንን ፡ ሞት
|