በአዝመራ ፡ ጊዜ ፡ መኝታ (Beazmera Gizie Megneta) - ታምራት ፡ ኃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ በአዝመራ ፡ ጊዜ ፡ መኝታ ፡ በጽሞና ፡ ጊዜ ፡ ጫጫታ
የሰልፍ ፡ ነው ፡ የድል ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ እልልታ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ማስተዋልን ፡ ስጠን ፡ ጊዜ ፡ እንዳያመልጠን

መከራው ፡ እግሩን ፡ ከማውጣቱ ፡ አቆምን ፡ መንበርከክ ፡ በፊቱ
የጸሎት ፡ መሰዊያ ፡ አፈረስን ፡ መስሎናል ፡ ሰማይ ፡ የደረስን
የምድረበዳው ፡ ትውልድ ፡ በውነ ፡ በወጉ ፡ አያውቅም ፡ ፡ ጦርነት
መሬትን ፡ አልረገጠም ፡ በእግሩ ፡ አታሎት ፡ እሩጫው ፡ ግርግሩ

አዝ፦ በአዝመራ ፡ ጊዜ ፡ መኝታ ፡ በጽሞና ፡ ጊዜ ፡ ጫጫታ
የሰልፍ ፡ ነው ፡ የድል ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ እልልታ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ማስተዋልን ፡ ስጠን ፡ ጊዜ ፡ እንዳያመልጠን

እርስ ፡ በርስ ፡ እየተሟሟቅን ፡ ነፍሳትን ፡ ተዘርፈን ፡ አለቅን
መርከቡ ፡ መልህቁን ፡ ዘርግቶ ፡ ይጣራል ፡ ተሳፋሪ ፡ ጠፍቶ
ይቺ ፡ አለም ፡ ካልደረስንላት ፡ ጨውና ፡ ብርሀን ፡ የላት
ህመሟ ፡ ሄደ ፡ እየቀጠለ ፡ መድሀኒት ፡ በእጃችን ፡ አለ

አዝ፦ በአዝመራ ፡ ጊዜ ፡ መኝታ ፡ በጽሞና ፡ ጊዜ ፡ ጫጫታ
የሰልፍ ፡ ነው ፡ የድል ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ እልልታ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ማስተዋልን ፡ ስጠን ፡ ጊዜ ፡ እንዳያመልጠን

ተባባልን ፡ እኔ ፡ ካንተ ፡ አላንስም ፡ ታወቅን ፡ ጌታ ፡ ባልሰጠን ፡ ሥም
ተራራቅን ፡ አጥር ፡ እያጠበቅን ፡ ለፍቅር ፡ ክፍያ ፡ ጠየቅን
በእልህ ፡ ሳይሰፋ ፡ ገደሉ ፡ ለበደልን ፡ ላጎደልነው ፡ ሁሉ
ንስሀ ፡ እንገባለን ፡ ፊትህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ይምጣልን ፡ ምህረትህ