አንድ ፡ ነገር ፡ አውቃለሁ (And Neger Awqalehu) - ታምራት ፡ ኃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታምራት ፡ ኃይሌ
(Tamrat Haile)

Lyrics.jpg


(8)

ኢየሱስ ፡ ነካኝ ፡ በድንገት
(Eyesus Nekagn Bedenget)

ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 15:03
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ኃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

ፀጋህን ፡ እንጂ ፡ ጽድቄን ፡ አልቆጥር
ከሰጠኸኝ ፡ በላይ ፡ ምንም ፡ አልጨምር
የማልጠቅም ፡ ባርያ ፡ ታሪክ ፡ የሌለኝ
አንድ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ አውቃለው ፡ ኢየሱስ ፡ እንዳዳነኝ

አዝ፦ አንድ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ አውቃለው ፡ ኢየሱስ ፡ ወዶኛል (፫x)
ማንስ ፡ ይከሰኛል
አንድ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ አውቃለው ፡ ኢየሱስ ፡ ወዶኛል (፫x)
ማን ፡ ይቃወመኛል

ሞትና ፡ እርግማን ፡ ተጭኖኝ ፡ ነበር
ነፍሴን ፡ አጉብጧት ፡ የሀጥያት ፡ ቀንበር
የዓለም ፡ ብርሀን ፡ ኢየሱስ ፡ ሲመጣ
ጨለማዬ ፡ ተወገደ ፡ ለእኔም ፡ ብርሀን ፡ ወጣ

አዝ፦ አንድ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ አውቃለው ፡ ኢየሱስ ፡ ወዶኛል (፫x)
ማንስ ፡ ይከሰኛል
አንድ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ አውቃለው ፡ ኢየሱስ ፡ ወዶኛል (፫x)
ማን ፡ ይቃወመኛል

አድራሻ ፡ የለኝ ፡ መነሻ ፡ ስፍራ
ሥሜ ፡ አይታወቅ ፡ ዘሬ ፡ አይጠራ
እንዳላሰብኩት ፡ በውን ፡ በህልሜ
ከነአብርሀም ፡ ከነዳዊት ፡ ተመዝግቧል ፡ ሥሜ

አዝ፦ አንድ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ አውቃለው ፡ ኢየሱስ ፡ ወዶኛል (፫x)
ማንስ ፡ ይከሰኛል
አንድ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ አውቃለው ፡ ኢየሱስ ፡ ወዶኛል (፫x)
ማን ፡ ይቃወመኛል

ብርሀኔና ፡ መድኃኒቴ ፡ ነው
ታዲያ ፡ እሱን ፡ አልፎ ፡ ሚነካኝ ፡ ማነው
ማንስ ፡ ቢመጣ ፡ ምን ፡ ያደርገኛል
የጸና ፡ ግንብ ፡ የእሳት ፡ አጥር ፡ ኢየሱስ ፡ ሆኖኛል

አዝ፦ አንድ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ አውቃለው ፡ ኢየሱስ ፡ ወዶኛል (፫x)
ማንስ ፡ ይከሰኛል
አንድ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ አውቃለው ፡ ኢየሱስ ፡ ወዶኛል (፫x)
ማን ፡ ይቃወመኛል

ከተደረገው ፡ ከሆነው ፡ ነገር
ጥቂቱም ፡ አይገባኝም ፡ ነበር
ሞልቶ ፡ እስከሚፈስ ፡ አየሁ ፡ ምህረቱን
ሁሉ ፡ ከእርሱ ፡ ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ ለእርሱ ፡ ክብር ፡ ይሁን

አዝ፦ አንድ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ አውቃለው ፡ ኢየሱስ ፡ ወዶኛል (፫x)
ማንስ ፡ ይከሰኛል
አንድ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ አውቃለው ፡ ኢየሱስ ፡ ወዶኛል (፫x)
ማን ፡ ይቃወመኛልአዝሀሌሉ ፡ ሀሌሉያ (፬x)
ክብር ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይሁን

ሁሉን ፡ የሚገዛ ፡ ስራው ፡ ታላቅና ፡ ድንቅ
ይገባዋል ፡ ለዘለዓለም ፡ እኛ ፡ ልናንስ ፡ እርሱ ፡ ሊልቅ
በመንገዱ ፡ ጻድቅ ፡ በፍርዱ ፡ እውነተኛ
ለቃሉ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ለስሙ ፡ ቀናተኛ

አዝሀሌሉ ፡ ሀሌሉያ (፬x)
ክብር ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይሁን

ከትንሳኤ ፡ በኩር ፡ ከፍጥረት ፡ መጀመሪያ
አልፋና ፡ ኦሜጋ ፡ መክፈቻና ፡ መዝጊያ
የቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ ራስ ፡ ያለና ፡ የሚመጣ
የጌቶች ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ነው

አዝሀሌሉ ፡ ሀሌሉያ (፬x)
ክብር ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይሁን

የርስታችን ፡ መያዢያ ፡ ለቤዛም ፡ ቀን ፡ ያተመን
ወደ ፡ እውነት ፡ የሚመራን ፡ በመከራም ፡ ሚያቆመን
በሀይሉ ፡ የሞላ ፡ ስጦታውን ፡ ያደለን
ከሰማይ ፡ የተላከ ፡ መንፈስ ፡ ቅድስ ፡ አለን

አዝሀሌሉ ፡ ሀሌሉያ (፬x)
ክብር ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይሁን

እግዚአብሔር ፡ አብ ፡ ልጁን ፡ ሰጠን ፡ እግዚአብሄር ፡ ወልድ ፡ እራሱን ፡ ሰጠን
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ቃሉን ፡ ሰጠን ፡ ቃሉም ፡ እኛን ፡ ለወጠ
ቸር ፡ አምላክ ፡ ባለጸጋ ፡ ዘወትር ፡ እጁን ፡ የዘረጋ
አያልቅበት ፡ ሁሌ ፡ ሙሉ ፡ ሀሌ ፡ ሀሌሉያ ፡ በሉ

አዝሀሌሉ ፡ ሀሌሉያ (፬x)
ክብር ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይሁንአዝ፦ አንድ ፡ ሰው ፡ ነካኝ ፡ በድንገት ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ነካኝ
እስራት ፡ ነበረኝ ፡ ፈታኝ ፡ ድካም ፡ ነበረኝ ፡ አነቃኝ
ጥማት ፡ ነበረኝ ፡ አረካኝ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ነካኝ

በርጠሚዎስ ፡ እኔነኝ ፡ ዘመድ ፡ የራቀኝ
እድሜ ፡ ልኬን ፡ በልመና ፡ አለም ፡ ያወቀኝ
የመንገድ ፡ ጉቶ ፡ እንቅፋት ፡ ሁሉም ፡ ሲሰድበኝ
እኔም ፡ ወግ ፡ ሊደርሰኝ ፡ ሆነ ፡ አምላክ ፡ ሊያስበኝ
የዳዊት ፡ ልጅ ፡ ሆይ ፡ ና ፡ ማረኝ ፡ ብዬ ፡ ብጣራ
ኢየሱስ ፡ መጣ ፡ ዳሰሰኝ ፡ አይኔን ፡ አበራ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ነካኝ ፡ በድንገት ፡ ኢየሱስ ፡ ነካኝ
እስራት ፡ ነበረኝ ፡ ፈታኝ ፡ ድካም ፡ ነበረኝ ፡ አነቃኝ
ጥማት ፡ ነበረኝ ፡ አረካኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነካኝ

ሽባ ፡ ነበረ ፡ ማይሰራ ፡ እግሬና ፡ እጄ
ሰላሳ ፡ ስምንት ፡ አመታት ፡ ተቆራምጄ
መላክ ፡ ሲመጣ ፡ ውሀውን ፡ ሲያንቀሳቅሰው
ቀድሞ ፡ የደረሰ ፡ ሲፈታ ፡ ሲሄድ ፡ ስንት ፡ ሰው
በድሌ ፡ ሳዝን ፡ በሰው ፡ ዘንድ ፡ እንደተረሳው
ኢየሱስ ፡ መጣ ፡ አስነሳኝ ፡ እኔም ፡ ተነሳው

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ነካኝ ፡ በድንገት ፡ ኢየሱስ ፡ ነካኝ
እስራት ፡ ነበረኝ ፡ ፈታኝ ፡ ድካም ፡ ነበረኝ ፡ አነቃኝ
ጥማት ፡ ነበረኝ ፡ አረካኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነካኝ

ለአስራ ፡ ሁለት ፡ አመታት ፡ እንባ ፡ እንደ ፡ ጅረት
ባለ ፡ መድሃኒት ፡ አልቀረኝ ፡ ስንት ፡ ሀገር ፡ ዙረት
ትርምስ ፡ አየሁ ፡ በድንገት ፡ ሳልፍ ፡ በመንገዱ
በብዙ ፡ ሺዎች ፡ መካከል ፡ ተከቧል ፡ አንዱ
ጌታ ፡ መሆኑን ፡ አውቄ ፡ ልብሱን ፡ ብነካ
መከራዬ ፡ በድንገት ፡ ምንጩ ፡ ተዘጋ