አምንሃለሁ (Amnehalehu) - ታምራት ፡ ኃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታምራት ፡ ኃይሌ
(Tamrat Haile)

Lyrics.jpg


(8)

ኢየሱስ ፡ ነካኝ ፡ በድንገት
(Eyesus Nekagn Bedenget)

ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 8:00
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ኃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

ፀጋህ ፡ ለእኔ ፡ በዝቶ ፡ እዚህ ፡ ደርሻለሁ
አንተ ፡ ከቆምክልኝ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ እሻለሁ
የገፋኝ ፡ ተገፍቶ ፡ የወጋኝ ፡ ተወጋ
ያልያዝኩትን ፡ ልያዝ ፡ እጆቼን ፡ ልዘርጋ
ባለሁበት ፡ አልሂድ ፡ ጊዜ ፡ አይለፍብኝ
እስቲ ፡ ከመንፈስህ ፡ እፍ ፡ በልብኝ

አዝ፦ አምንሀለው ፡ ጌታ ፡ አምንሀለው
ቃልህን ፡ ስታከብር ፡ አይቻለው
አምንሀለው ፡ ጌታ ፡ አምንሀለው

ከግብጽ ፡ ወጥቼ ፡ ምድረበዳ ፡ ዘለኩ
ባህር ፡ ተሻግሬ ፡ ዮርዳኖስን ፡ አለፍኩ
እያሪኮ ፡ በራፍ ፡ ቆሜ ፡ ለምን ፡ ላልቅስ
የትላንቱን ፡ ጌታ ፡ ልታመን ፡ ይልቅስ
የግብጽን ፡ ሰራዊት ፡ ባህር ፡ ያሰጠመ
እግዚአብሄር ፡ ብርቱ ፡ ነው ፡ ዛሬም ፡ አልደከመም

አዝ፦ አምነዋለው ፡ ጌታን ፡ አምነዋለው
ቃልኪዳኑን ፡ ሲያከብር ፡ አይቻለው (፪x)
አምነዋለው ፡ ጌታን ፡ አምነዋለው

የኤናቄል ፡ ልጆች ፡ ቁመናቸው ፡ ሎጋ
ውስጣቸው ፡ ባዶ ፡ ነው ፡ በእምነት ፡ ልጠጋ
በእነርሱ ፡ አይን ፡ ስታይ ፡ አንበጣ ፡ መስላለው
በውስጤ ፡ ያለው ፡ ግን ፡ ኃያል ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
እስከመቼ ፡ ድረስ ፡ ፈርቼ ፡ ልኑር
ተሻግሬ ፡ ልውረስ ፡ የተስፋይቱን ፡ ምድር

አዝ፦ አምነዋለው ፡ ጌታን ፡ አምነዋለው
ቃልኪዳኑን ፡ ሲያከብር ፡ አይቻለው (፪x)
አምነዋለው ፡ ጌታን ፡ አምነዋለው

እምነት ፡ ከመስማት ፡ ነው ፡ መስማትም ፡ በቃሉ
ለሚመረምሩት ፡ መልስ ፡ አለው ፡ ለሁሉ
ቃሉን ፡ እያነበብኩ ፡ ተስፋውን ፡ ባላምን
ጊዜ ፡ ማጥፋት ፡ እንጂ ፡ መመላለስ ፡ ለምን
በአባቶቼ ፡ ዘመን ፡ ድንቅን ፡ ያደረገው
የጠራኝ ፡ እግዚአብሄር ፡ የጌቶች ፡ ጌታ ፡ ነው

አዝ፦ አምነዋለው ፡ ጌታን ፡ አምነዋለው
ቃልኪዳኑን ፡ ሲያከብር ፡ አይቻለው (፪x)
አምነዋለው ፡ ጌታን ፡ አምነዋለውከስሞች ፡ በላይ ፡ ስሙ ፡ ሀያል ፡ በሰማይ ፡ በምድር ፡ ሁሉን ፡ ያያል
የተዋረደን ፡ ከፍ ፡ ያደርጋል ፡ ታናናሾችን ፡ ያሳድጋል
ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው ፡ በችሎታው ፡ ከልካይ ፡ የለውም ፡ የሚገታው
ምስጋና ፡ ክብር ፡ ሞገስ ፡ ለርሱ ፡ ለዘለዓለም ፡ ለንጉሱ

አዝ፦ መውደቅ ፡ ለጠላቴ ፡ መዋረድ ፡ ለሰይጣን
መድከም ፡ ለስጋዬ ፡ መሸነፍ ፡ ለዓለም
ክብር ፡ ግን ፡ ለኢየሱስ ፡ ይሁን ፡ ለዘለዓለም

በሰማይ ፡ ይሁን ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ አቻ ፡ የለውም ፡ እሱን ፡ መሳይ
እርሱ ፡ ብቻውን ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ታናሽም ፡ ታላቅ ፡ የሌለው
ስጋ ፡ በፊቱ ፡ ይዋረድ ፡ ዲያቢሎስ ፡ አይቶ ፡ ይንደድ
ዓለም ፡ በሞላ ፡ ትስገድ ፡ ለርሱ ፡ ክብር ፡ ይሁንለት ፡ ለንጉሱ

አዝ፦ መውደቅ ፡ ለጠላቴ ፡ መዋረድ ፡ ለሰይጣን
መድከም ፡ ለስጋዬ ፡ መሸነፍ ፡ ለዓለም
ክብር ፡ ግን ፡ ለኢየሱስ ፡ ይሁን ፡ ለዘለዓለም

አሶር ፡ ቢነሳ ፡ በበትሩ ፡ እነ ፡ ሰናኬ ፡ ቢፎክሩ
ናቡከደነጾር ፡ ቢኮራ ፡ አንበሳው ፡ ፈርኦን ፡ ቢያጓራ
ሁሉም ፡ እንደጥላ ፡ አለፉ ፡ ከእግሩ ፡ በታች ፡ ተደፉ
እያሸነፈ ፡ እየረታ ፡ አለ ፡ ይኖራል ፡ የኛ ፡ ጌታ ፡

አዝ፦ መውደቅ ፡ ለጠላቴ ፡ መዋረድ ፡ ለሰይጣን
መድከም ፡ ለስጋዬ ፡ መሸነፍ ፡ ለዓለም
ክብር ፡ ግን ፡ ለኢየሱስ ፡ ይሁን ፡ ለዘለዓለም

ጌታ ፡ ከፍይበል ፡ እኛ ፡ ዝቅ ፡ ሊገን ፡ ሊከብር ፡ ሊልቅ
እርሱ ፡ ይውረሰው ፡ ሁሉን ፡ ቦታ ፡ በሁሉም ፡ ነገር ፡ ይሁን ፡ ጌታ
ይዘምርለት ፡ አፋችን ፡ ያጨብጭብለት ፡ እጃችን
ዕልልታው ፡ ይድመቅ ፡ በሆታ ፡ ይህም ፡ ያንሰዋል ፡ ለጌታ