From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
የተወደዳችሁ ፡ አድማጮቼ ፣
ከዚህ ፡ ቀጥሎ ፡ የምታደምጡት ፡ መዝሙር ፡
በሉቃስ ፡ ወንጌል ፡ ምእራፍ ፡ ፲፭ ፡ ከቁጥር ፡ ፲፩ - ፳፬ ፡
ድረስ ፡ በተፃፈው ፡ የኮብላይ ፡ ልጅ ፡ ታሪክ ፡ የተወሰደ ፡
መሆኑን ፡ እያስታወስኩ ፡ በዚህ ፡ ታሪክ ፡ ምሳሌነት ፡
የእግዚአብሔር ን፡ አባታዊ ፡ እና ፡ ዘለዓለማዊ ፡ ፍቅር ፡
አሳስባችኋለሁ ። በምታደምጧቸው ፡ ዝማሬዎች ፡ ሁሉ ፡
እግዚአብሔር ፡ ይባርካችሁ ። አሜን ።
አዝ፦ ወደ ፡ አባቴ ፡ ወደ ፡ ቀድሞ ፡ ቤቴ ፡ እመለሳለሁ
እንደ ፡ ልጁም ፡ ባይሆን ፡ እንደ ፡ ባሪያው ፡ እኖራለሁ (፪x)
መስሎኝ ፡ ነበር ፡ እኔ ፡ እራሴን ፡ የገዛሁ
ንብረቴን ፡ ሰብስቤ ፡ ሩቅ ፡ ሃገር ፡ ተነሳሁ
ለካስ ፡ ልጅ ፡ ኖሬያለሁ ፡ ምራቄን ፡ ያልዋጥኩኝ
ለወፍ ፡ ለአሞራ ፡ ያለኝን ፡ በተንኩኝ
ጉልበቴም ፡ ደከመ ፡ ሕይወቴም ፡ ባከነ
ለካስ ፡ አባት ፡ ኖሮዋል ፡ ጉዴን ፡ የሸፈነ
አዝ፦ ወደ ፡ አባቴ ፡ ወደ ፡ ቀድሞ ፡ ቤቴ ፡ እመለሳለሁ
እንደ ፡ ልጁም ፡ ባይሆን ፡ እንደ ፡ ባሪያው ፡ እኖራለሁ (፪x)
ወዳጄ ፡ ነበረ ፡ ካለኝ ፡ ያካፈልኩት
ያጣሁ ፡ የነጣሁ ፡ እለት ፡ ከቦታው ፡ አጣሁት
ሁሉም ፡ በር ፡ ዘግቶ ፡ አላውቅህም ፡ አለኝ
የሚያዝንልኝ ፡ አጣሁ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ አገለለኝ
አየሁ ፡ ተገነዘብኩ ፡ ወዳጅ ፡ ማንነቱን
ማን ፡ ይሆንለታል ፡ ለሰው ፡ እንደ ፡ አባቱ?
አዝ፦ ወደ ፡ አባቴ ፡ ወደ ፡ ቀድሞ ፡ ቤቴ ፡ እመለሳለሁ
እንደ ፡ ልጁም ፡ ባይሆን ፡ እንደ ፡ ባሪያው ፡ እኖራለሁ (፪x)
ሰርቼ ፡ እንዳልበላ ፡ ጨርሶ ፡ የለኝ ፡ ሞያ
ተደብቄ ፡ ኖርኩኝ ፡ በአባቴ ፡ ጉያ
ጉዴ ፡ ተገለጠ ፡ ታየ ፡ ገበናዬ ፡
ከእሪያዎች ፡ ጋር ፡ ሆነ ፡ መዋያዬ
ዘበኝነት ፡ አጣሁ ፡ ጠፋኝ ፡ መላ ፡ ቅጡ
ለካስ ፡ ማእረግ ፡ የለም ፡ ከአባት ፡ ቤት ፡ ከወጡ
አዝ፦ ወደ ፡ አባቴ ፡ ወደ ፡ ቀድሞ ፡ ቤቴ ፡ እመለሳለሁ
እንደ ፡ ልጁም ፡ ባይሆን ፡ እንደ ፡ ባሪያው ፡ እኖራለሁ (፪x)
እኔን ፡ ያየኝ ፡ ይቀጣ ፡ ይማር ፡ ከሕይወቴ
እርቃናዬን ፡ ቀረሁ ፡ በአባካኝነቴ
ሳለሁ ፡ ባባቴ ፡ ቤት ፡ ወዜን ፡ ያየ ፡ ማነው?
ያስብ ፡ ጠንቀቅ ፡ ይበል
ይህ ፡ ዓለም ፡ ክፉ ፡ ነው ፡ አጫርሶ ፡ ዝም ፡ ይላል
ምንም ፡ ይሁን ፡ ምንም ፡ የአባት ፡ ቤት ፡ ይሻላል
አዝ፦ ወደ ፡ አባቴ ፡ ወደ ፡ ቀድሞ ፡ ቤቴ ፡ እመለሳለሁ
እንደ ፡ ልጁም ፡ ባይሆን ፡ እንደ ፡ ባሪያው ፡ እኖራለሁ (፪x)
አዋጅን ፡ የምትሰማ ፡ ያለህ ፡ የትም ፡ ቦታ
ጨለማ ፡ የዋጠህ ፡ የጠፋህ ፡ ከጌታ
እንጀራውን ፡ በልተህ ፡ ፈውሱን ፡ ተቀብለህ
ድርሻህን ፡ በመውሰድ ፡ የሄድከው ፡ ኮብልለህ
እስኪ ፡ መለስ ፡ በል ፡ ወደ ፡ ጥንቱ ፡ ቤትህ
አይጨክንብህም ፡ ርህሩህ ፡ ነው ፡ አባትህ
ለጣትህ ፡ ቀለበት ፡ ለእግርህ ፡ ጫማ
ያጐናፅፍሃል ፡ በመንፈሱ ፡ ሸማ
ፍሪዳ ፡ ይታረድ ፡ ወገን ፡ ደስ ፡ ይበለው
ለነገ ፡ አታሳድር ፡ መዳንህ ፡ ዛሬ ፡ ነው
አዝ፦ ወደ ፡ አባቴ ፡ ወደ ፡ ቀድሞ ፡ ቤቴ ፡ እመለሳለሁ
እንደ ፡ ልጁም ፡ ባይሆን ፡ እንደ ፡ ባሪያው ፡ እኖራለሁ (፪x)
|