ማን ፡ ነው ፡ ያነጋው (Man New Yanegaw) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ታምራት ፡ ሃይሌ
(Tamrat Haile)

Lyrics.jpg


(6)

ኢየሱስ ፡ ገናና ፡ ነው
(Eyesus Genana New)

ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:39
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ሃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

አዝ፦ ማነው ፡ ያነጋው ፡ ሌሊቱን
ማነው ፡ ያጠፋው ፡ እሳቱን
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ (፪x)

በአንድ ፡ መንገድ ፡ የመጡ ፡ በብዙ ፡ በሺህ ፡ ሲወጡ
እየወደቁ ፡ ሲነሱ ፡ ክብርን ፡ ለጌታ ፡ ሲሰጡ
የናቀኝ ፡ ሁሉ ፡ ሲያከብረኝ ፡ በክብር ፡ ስሜ ፡ ሲጠራኝ
ዕድሜ ፡ ሰጥተኸኝ ፡ አየሁኝ ፡ የአንተ ፡ መሆኔ ፡ አኮራኝ (፪x)

አዝ፦ ማነው ፡ ያነጋው ፡ ሌሊቱን
ማነው ፡ ያጠፋው ፡ እሳቱን
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ (፪x)

ከባቢሎን ፡ ወንዞች ፡ ማዶ ፡ ከምርኮ ፡ ከስር ፡ ከተማ
የመውጣት ፡ ነገር ፡ ሲነገር ፡ የነፃነት ፡ ድምፅ ፡ ሲሰማ
ደወል ፡ ሲመታ ፡ በድንገት ፡ ኧረ ፡ የማን ፡ልብ ፡ አመነ
ምን ፡ ያቅትሃል ፡ ጌታችን ፡ አንተ ፡ ስላልከው ፡ ግን ፡ ሆነ (፪x)

አዝ፦ ማነው ፡ ያነጋው ፡ ሌሊቱን
ማነው ፡ ያጠፋው ፡ እሳቱን
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ (፪x)

በባእድ ፡ ምድር ፡ እያለን ፡ የታመቀውን ፡ እሳት
ጌታ ፡ ሊያነደው ፡ ጀመረ ፡ አዲስን ፡ ምእራፍ ፡ ሊከፍት
ከዛፍ ፡ ወረደ ፡ ማሲንቆ ፡ ከዛፍ ፡ ወረደ ፡ በገና
የፅዮን ፡ ዝማሬ ፡ ልንዘምር ፡ አዲሱን ፡ ቅኔ ፡ ምሥጋና (፪x)

አዝ፦ ማነው ፡ ያነጋው ፡ ሌሊቱን
ማነው ፡ ያጠፋው ፡ እሳቱን
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ (፪x)

እያለቀስን ፡ ወጥተናል ፡ በሃዘን ፡ ዘርን ፡ ዘርተናል
በምድር ፡ በሠማይ ፡ መካከል ፡ እንባችንን ፡ ረጭተናል
የዜማ ፡ ጊዜ ፡ ደረሰ ፡ ነዶአችንን ፡ ይዘን ፡ መጥተናል
በውዳችን ፡ ተደግፈን ፡ ከምድረ ፡ በዳ ፡ ወጥተናል (፪x)

አዝ፦ ማነው ፡ ያነጋው ፡ ሌሊቱን
ማነው ፡ ያጠፋው ፡ እሳቱን
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ (፪x)

ጌታ ፡ ምርኮያችንን ፡ ሲመልስ ፡ ለቅሶ ፡ በመዝሙር ፡ ሲተካ
ቃላችን ፡ ውስን ፡ ምድራዊ ፡ ደስታችን ፡ በምን ፡ ይለካ
አፋችንን ፡ በሳቅ ፡ ሞላ ፡ አንደበታችን ፡ ምሥጋና
ሁሉን ፡ ውብ ፡ አድርጓል ፡ የታሪክ ፡ ጌታ ፡ ነውና (፪x)

አዝ፦ ማነው ፡ ያነጋው ፡ ሌሊቱን
ማነው ፡ ያጠፋው ፡ እሳቱን
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ (፪x)