ማን ፡ ነው ፡ ያነጋው== ንዑስ ክፍል ==gaው (Man New Yanegaw) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታምራት ፡ ሃይሌ
(Tamrat Haile)

Lyrics.jpg


(6)

ኢየሱስ ፡ ገናና ፡ ነው
(Eyesus Genana New)

ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:39
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ሃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)


አዝ፦ (ማነው ፡ ያነጋው ፡ ሌሊቱን? ፡ማነው ፡ ያጠፋው ፡ እሳቱን?
(ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ) ፡ ፪X ፡ (፪X)

በአንድ ፡ መንገድ ፡ የመጡ ፡ በብዙ ፡ በሺህ ፡ ሲወጡ
እየወደቁ ፡ ሲነሱ ፡ ክብርን ፡ ለጌታ ፡ ሲሰጡ ፡
የናቀኝ ፡ ሁሉ ፡ ሲያከብረኝ ፡ በክብር ፡ ስሜ ፡ ሲጠራኝ
ዕድሜ ፡ ሰጥተኸኝ ፡ አየሁኝ ፡ (ያንተ ፡ መሆኔ ፡ አኮራኝ) ፡ ፪X

አዝ፦ (ማነው ፡ ያነጋው ፡ ሌሊቱን? ፡ማነው ፡ ያጠፋው ፡ እሳቱን?
(ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ) ፡ ፪X ፡ (፪X)

ከባቢሎን ፡ ወንዞች ፡ ማዶ ፡ ከምርኮ ፡ ከስር ፡ ከተማ
የመውጣት ፡ ነገር ፡ ሲነገር ፡የነፃነት ፡ ድምፅ ፡ ሲሰማ
ደወል ፡ ሲመታ ፡ በድንገት ፡ ኧረ ፡ የማን ፡ልብ ፡ አመነ?
ምን ፡ ያቅትሃል ፡ ጌታችን? ፡ (አንተ ፡ ስላልከው ፡ ግን ፡ ሆነ) ፡ ፪X

አዝ፦ (ማነው ፡ ያነጋው ፡ ሌሊቱን? ፡ማነው ፡ ያጠፋው ፡ እሳቱን?
(ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ) ፡ ፪X ፡ (፪X)

በባእድ ፡ ምድር ፡ እያለን ፡ የታመቀውን ፡ እሳት
ጌታ ፡ ሊያነደው ፡ ጀመረ ፡ አዲስን ፡ ምእራፍ ፡ ሊከፍት
ከዛፍ ፡ ወረደ ፡ ማሲንቆ ፡ ከዛፍ ፡ ወረደ ፡ በገና
የፅዮን ፡ ዝማሬ ፡ ልንዘምር ፡ (አዲሱን ፡ ቅኔ ፡ ምሥጋና) ፡ ፪X

አዝ፦ (ማነው ፡ ያነጋው ፡ ሌሊቱን? ፡ማነው ፡ ያጠፋው ፡ እሳቱን?
(ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ) ፡ ፪X ፡ (፪X)

እያለቀስን ፡ ወጥተናል ፡ በሃዘን ፡ ዘርን ፡ ዘርተናል
በምድር ፡ በሠማይ ፡ መካከል ፡ እንባችንን ፡ ረጭተናል
 የዜማ ፡ ጊዜ ፡ ደረሰ ፡ ነዶአችንን ፡ ይዘን ፡ መጥተናል
በውዳችን ፡ ተደግፈን ፡ (ከምድረ ፡ በዳ ፡ ወጥተናል) ፡ ፪X

አዝ፦ (ማነው ፡ ያነጋው ፡ ሌሊቱን? ፡ማነው ፡ ያጠፋው ፡ እሳቱን?
(ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ) ፡ ፪X ፡ (፪X)

ጌታ ፡ ምርኮያችንን ፡ ሲመልስ ፡ ለቅሶ ፡ በመዝሙር ፡ ሲተካ
ቃላችን ፡ ውስን ፡ ምድራዊ ፡ ደስታችን ፡ በምን ፡ ይለካ?
አፋችንን ፡ በሳቅ ፡ ሞላ ፡ አንደበታችን ፡ ምሥጋና
ሁሉን ፡ ውብ ፡ አድርጓል ፡ (የታሪክ ፡ ጌታ ፡ ነውና) ፡ ፪X

አዝ፦ (ማነው ፡ ያነጋው ፡ ሌሊቱን? ፡ማነው ፡ ያጠፋው ፡ እሳቱን?
(ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክንደ ፡ ብርቱ) ፡ ፪X ፡ (፪X)