ኢየሱስ ፡ ገናና ፡ ነው (Eyesus Genana New) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታምራት ፡ ሃይሌ
(Tamrat Haile)

Lyrics.jpg


(6)

ኢየሱስ ፡ ገናና ፡ ነው
(Eyesus Genana New)

ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 10:21
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ሃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

ክብሩን ፡ ሁሉ ፡ ትቶ ፡ ከሠማይ ፡ ወረደ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
የሰው ፡ ሥጋ ፡ ለብሶ ፡ ራሱን ፡ አዋረደ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
የእግዚአብሔር ፡ በግ ፡ ሆኖ ፡ በረት፡ ተወለደ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
የዋህ ፡ ትሁት ፡ ሆኖ ፡ እንደ ፡ በግ ፡ ታረደ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
ፈራጅ ፡ በሌለበት ፡ እውነተኛ ፡ ዳኛ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
የውርደት ፡ ሞት ፡ ሊሞት ፡ እንደወንጀለኛ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
በደሙ ፡ ቢነከር ፡ ቀራንዮ ፡ ተራራ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
መቃብሩም ፡ ቢሆን ፡ ከአመፀኞች ፡ ጋራ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
በሞተ ፡ ሰልስቱ ፡ ታሪክ ፡ ተለወጠ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
አይሰማ ፡ ሰምቶ ፡ ዓለም ፡ ደነገጠ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
መቃብሩን ፡ ከፈተ ፡ ማኅተሙን ፡ ፈታ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
ሞትን ፡ ድል ፡ አረገ ፡ የትንሳኤው ፡ ጌታ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና

አዝገናና ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና (፬x)
ተወዳዳሪ ፡ የለውምና
አቻ ፡ የሚሆነው ፡ የለውምና
ገናና ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና (፫x)

የሞት ፡ መርዶ ፡ ሰምተው ፡ በሃዘን ፡ የተዋጡ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
በትንሳኤው ፡ ብስራት ፡ ዕልልታ ፡ አቀለጡ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
አጠፋነው ፡ ብለው ፡ የዘፈኑ ፡ ሁሉ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
ትንሳኤውን ፡ ሲሰሙ ፡ ምድር ፡ ዋጪን ፡ አሉ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
በኢየሱስ ፡ ሰፈር ፡ ዕልልታ ፡ ሲሰማ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
በዲያብሎስ ፡ ሰፈር ፡ የሃዘን ፡ ጨለማ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
ከማሪያም ፡ ጀምሮ ፡ እስከ ፡ ቶማስ ፡ ድረስ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
በዐይን ፡ በማየት ፡ ደግሞም ፡ በመዳሰስ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
ኢየሱስ ፡ መነሳቱን ፡ አረጋገጡልን
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
ይህን ፡ ክቡር ፡ ታሪክ ፡ ፅፈው ፡ አስቀሩልን
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
አምነን ፡ የተቀበልን ፡ እኛም ፡ ተነስተናል
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
በኢየሱስ ፡ ትንሳኤ ፡ሞትን ፡ እረግጠናል

አዝገናና ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና (፬x)
ተወዳዳሪ ፡ የለውምና
አቻ ፡ የሚሆነው ፡ የለውምና
ገናና ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና (፫x)

የኢየሱስ ፡ ጌትነት ፡ በዚህ ፡ አላበቃም
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
ገና ፡ ይቀጥላል ፡ ታሪክ ፡ አልተዘጋም
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
ከትንሳኤው ፡ ኋላ ፡ አርባ ፡ ቀናት ፡ ኖሮ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
የቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ መሰረት ፡ አኑሮ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
ሰው ፡ ሆኖ ፡ የመጣው ፡ ጌታ ፡ ሆኖ ፡ ሄዷል
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
በውርደት ፡ የመጣው ፡ በክብር ፡ አርጓል
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
ዛሬም ፡ ሕያው ፡ ሆኖ ፡ በአብ ፡ ቀኝ ፡ አለልን
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
እያማለደልን ፡ ቤት ፡ እየሰራልን
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
ያኔ ፡ መጀመሪያ ፡ በግ ፡ ሆኖ ፡ የመጣው
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
ዳግም ፡ ሲመለስ ፡ ግን ፡ የጌታዎች ፡ ጌታ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
በመለከት ፡ ድምፅ ፡ በመላእክት ፡ አጀብ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
አብረን ፡ እንድንገባ ፡ ቶሎ ፡ እንመዝገብ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
ስለስሙ ፡ ብለው ፡ የተገፉ ፡ ሁሉ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
ኢየሱስ ፡ ሲከብር ፡ አብረው ፡ ይከብራሉ

አዝገናና ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና (፬x)
ተወዳዳሪ ፡ የለውምና
አቻ ፡ የሚሆነው ፡ የለውምና
ገናና ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና (፫x)

ዛሬም ፡ በዚህ ፡ ዘመን ፡ በሕይወቱ ፡ እያለ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
ካልካደ ፡ በስተቀር ፡ ያላየ ፡ ማን ፡ አለ?
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
ክህደትን ፡ አመፅን ፡ ከምድር ፡ ሲያጠፋ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
የእግዚአብሔር ፡ መንግሥት ፡ ድንበሯ ፡ ሲሰፋ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
በኢየሱስ ፡ ስም ፡ ስልጣን ፡ ወንጌሉ ፡ ሲሰበክ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
ምላስ ፡ ሲመሰክር ፡ ጉልበት ፡ ሲንበረከክ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
ታዲያ ፡ ለምንድነው ፡ ወገኔ ፡ የምትደክም?
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
ሕያው ፡ አምላክ ፡ እንጂ ፡ ግኡዝ ፡ አታመልክም
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
በዚህ ፡ አጭር ፡ ዘመኔ ፡ ኧረ ፡ ስንት ፡ አሳየኝ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
ለኢየሱስ ፡ ጌትነት ፡ እኔም ፡ ምስክር ፡ ነኝ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
አንቺም ፡ ምስክር ፡ ነሽ ፡ አንተም ፡ ምስክር ፡ ነህ
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና
ሁላችንም ፡ እንበለው ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው
ኦ ፡ ገናና ፡ ነው ፣ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና

አዝገናና ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና (፬x)
ተወዳዳሪ ፡ የለውምና
አቻ ፡ የሚሆነው ፡ የለውምና
ገናና ፡ ኢየሱስ ፡ ገናና (፫x)