Tamrat Haile/Eyesus Genana New/Bedenq Aterareh
ዘማሪ=ታምራት ሃይሌ ርዕስ በድንቅ አጠራርህ አልበም ኢየሱስ ገናና ነው Track 9 አዝ በድንቅ አጠራርህ የጠራኸኝ በእረፍት ውሃ ዘንድ የመራኸኝ በለመለመ መስክ ያሳደርከኝ በአለት ንቃቃት የሰወርከኝ ተግተህ የጠበከኝ እንዳልጠፋ መድሃኒዓለም ክብርህ ይስፋ በግብጻውያን በደል በዓመጻቸው ቁጣህ ከላይ ወርዶ ሲፈጃቸው ደምህ ተቀብቶ በመቃኔ ምክንያት ሆኖልኛል ለመዳኔ ተጠነቀክልኝ እንዳልጠፋ ዙፋንህ ከፍ ይበል ይንሰራፋ አዝ በድንቅ አጠራርህ የጠራኸኝ በእረፍት ውሃ ዘንድ የመራኸኝ በለመለመ መስክ ያሳደርከኝ በአለት ንቃቃት የሰወርከኝ ተግተህ የጠበከኝ እንዳልጠፋ መድሃኒዓለም ክብርህ ይስፋ በኮሬብ ተራራ በእሳት አምሳል ለነብዩ ሙሴ ተገልፀሃል በእኔም ልብ አንድደህ የፍቅር እሳት ምስኪኑን ሕይወቴን ስታጋያት አይቻለሁ እና እንዳቅሜ አመሰግናለው ይኸው ቆሜ አዝ በድንቅ ፡ አጠራርህ ፡ የጠራኸኝ በእረፍት ውሃ ዘንድ የመራኸኝ በለመለመ መስክ ያሳደርከኝ በአለት ንቃቃት የሰወርከኝ ተግተህ የጠበከኝ እንዳልጠፋ መድሃኒዓለም ክብርህ ይስፋ ከኃጤአቴ በቀር ከመርከሴ የማውቀው የለኝም ስለራሴ አንተን ግን አውቃለሁ ስታድንኝ የድሃ አደግ አባት ስትሆነኝ በፍቅር ይዘኸኛል በውዴታ እኔም ላመስግንህ በእልልታ (፪x) አዝ በድንቅ ፡ አጠራርህ ፡ የጠራኸኝ በእረፍት ውሃ ዘንድ የመራኸኝ በለመለመ መስክ ያሳደርከኝ በአለት ንቃቃት የሰወርከኝ ተግተህ የጠበከኝ እንዳልጠፋ መድሃኒዓለም ክብርህ ይስፋ አጋጣሚ አይደለም ያገናኘን እንደ አባት እና ልጅ ያቆራኘን ለእኔ ያሰብከው ያኔ ድሮ ዛሬ ተፈፀመ ዘመን ቆጥሮ ያረካህ እንደሆን ይኸው መልሴ ምስጋና እና ክብር ከውዳሴ አዝ በድንቅ አጠራርህ የጠራኸኝ በእረፍት ውሃ ዘንድ የመራኸኝ በለመለመ መስክ ያሳደርከኝ በአለት ንቃቃት የሰወርከኝ ተግተህ የጠበከኝ እንዳልጠፋ መድሃኒዓለም ክብርህ ይስፋ Insert non-formatted text here