ዓለም ፡ ሁሉ (Alem Hulu) - ታምራት ፡ ኃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታምራት ፡ ኃይሌ
(Tamrat Haile)

Lyrics.jpg


(6)

ኢየሱስ ፡ ገናና ፡ ነው
(Eyesus Genana New)

ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 7:21
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ኃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

አዝ፦ ዓለም ፡ ሁሉ ፡ በሽተኛ ፡ ሕመምተኛ
ግን ፡ መድሃኒት ፡ አለን ፡ እኛ ፡ ኑ ፡ ወደ ፡ እኛ
ሥሙ ፡ ኢየሱስ ፡ መድኃኒ ፡ ዓለም
እንደርሱ ፡ ያለ ፡ የትም ፡ የለም
ፀንቶ ፡ የሚኖር ፡ ለዘላለም (፪x)
እውነት ፡ ሕይወት ፡ መንገድ ፡ እርሱ
ለነፍስ ፡ መዳን ፡ ለሥጋ ፡ ፈውሱ
ድምፁን ፡ ስሙ ፡ ተመለሱ
ወደ ፡ እርሱ ፡ ኑ ፡ ዛሬውኑ (፪x)

የኦሪት ፡ ሕግ ፡ መተኪያ ፡ የነቢያት ፡ ትንቢት ፡ መሙያ
የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ መጀመሪያ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ሃሌሉያ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ሃሌሉያ
ድንግል ፡ ማሪያም ፡ ደስ ፡ ይበልሽ ፡ የአምላክ ፡ ፀጋ ፡ የሞላብሽ
የማህፀንሽ ፡ በኩር ፡ ፍሬ ፡ ያድነናል ፡ እስከ ፡ ዛሬ
ያድነናል ፡ እስከ ፡ ዛሬ
(፪x)

አዝ፦ ዓለም ፡ ሁሉ ፡ በሽተኛ ፡ ሕመምተኛ
ግን ፡ መድሃኒት ፡ አለን ፡ እኛ ፡ ኑ ፡ ወደ ፡ እኛ
ሥሙ ፡ ኢየሱስ ፡ መድኃኒ ፡ ዓለም
እንደርሱ ፡ ያለ ፡ የትም ፡ የለም
ፀንቶ ፡ የሚኖር ፡ ለዘላለም (፪x)
እውነት ፡ ሕይወት ፡ መንገድ ፡ እርሱ
ለነፍስ ፡ መዳን ፡ ለሥጋ ፡ ፈውሱ
ድምፁን ፡ ስሙ ፡ ተመለሱ
ወደ ፡ እርሱ ፡ ኑ ፡ ዛሬውኑ (፪x)

በባሕር ፡ ዳር ፡ በገሊላ ፡ በሞት ፡ አገር ፡ በሞት ፡ ጥላ
ተወለደ ፡ ብርሃን ፡ አብሪ ፡ የአስጨናቂውን ፡ ዘንግ ፡ ሰባሪ
የአስጨናቂውን ፡ ዘንግ ፡ ሰባሪ ፣ የአስጨናቂውን ፡ ዘንግ ፡ ሰባሪ
ሕፃን ፡ ተወልዶልናል ፡ ወንድ ፡ ልጅም ፡ ተሰጥቶናል
አለቅነት ፡ በጫንቃው ፡ ላይ ፡ እልል ፡ በሉ ፡ ምድር ፡ ሠማይ
ዕልል ፡ በሉ ፡ ምድር ፡ ሠማይ
(፪x)

አዝ፦ ዓለም ፡ ሁሉ ፡ በሽተኛ ፡ ሕመምተኛ
ግን ፡ መድሃኒት ፡ አለን ፡ እኛ ፡ ኑ ፡ ወደ ፡ እኛ
ሥሙ ፡ ኢየሱስ ፡ መድኃኒ ፡ ዓለም
እንደርሱ ፡ ያለ ፡ የትም ፡ የለም
ፀንቶ ፡ የሚኖር ፡ ለዘላለም (፪x)
እውነት ፡ ሕይወት ፡ መንገድ ፡ እርሱ
ለነፍስ ፡ መዳን ፡ ለሥጋ ፡ ፈውሱ
ድምፁን ፡ ስሙ ፡ ተመለሱ
ወደ ፡ እርሱ ፡ ኑ ፡ ዛሬውኑ (፪x)

ሳይጠበው ፡ ምድርን ፡ ሳይሞላ ፡ ሰው ፡ እርስ ፡ በእርሱ ፡ የሚባላ
ጦር ፡ የሚመዝ ፡ በወንድሙ ፡ ፈውስ ፡ አጥቶ ፡ ነው ፡ ለሕመሙ
ፈውስ ፡ አጥቶ ፡ ነው ፡ ለሕመሙ
ድንቅ ፡ መካር ፡ ኃያል ፡ አምላክ ፡ ደግሞም ፡ የዘለዓለም ፡ አባት
ስሙም ፡ የሰላም ፡ አለቃ ፡ እርሱን ፡ ብንይዝ ፡ ችግር ፡ በቃ
እርሱን ፡ ብንይዝ ፡ ችግር ፡ በቃ
(፪x)

አዝ፦ ዓለም ፡ ሁሉ ፡ በሽተኛ ፡ ሕመምተኛ
ግን ፡ መድሃኒት ፡ አለን ፡ እኛ ፡ ኑ ፡ ወደ ፡ እኛ
ሥሙ ፡ ኢየሱስ ፡ መድኃኒ ፡ ዓለም
እንደርሱ ፡ ያለ ፡ የትም ፡ የለም
ፀንቶ ፡ የሚኖር ፡ ለዘላለም (፪x)
እውነት ፡ ሕይወት ፡ መንገድ ፡ እርሱ
ለነፍስ ፡ መዳን ፡ ለሥጋ ፡ ፈውሱ
ድምፁን ፡ ስሙ ፡ ተመለሱ
ወደ ፡ እርሱ ፡ ኑ ፡ ዛሬውኑ (፫x)

ፈውስ ፡ በሌለው ፡ በሽታ ፡ ዓለማችን ፡ ስትመታ
ሰው ፡ እንደ ፡ እቃ ፡ የትም ፡ ሲጣል ፡ ከዚህ ፡ በላይ ፡ ምን ፡ ሊመጣ
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ምን ፡ ሊመጣ
የምሥራች ፡ ላብስራችሁ ፡ መድሃኒቱን ፡ ልንገራችሁ
ኢየሱስን ፡ እንቀበል ፡ አንሰቃይ ፡ እፎይ ፡ እንበል
አንሰቃይ ፡ እፎይ ፡ እንበል
(፪x)

አዝ፦ ዓለም ፡ ሁሉ ፡ በሽተኛ ፡ ሕመምተኛ
ግን ፡ መድሃኒት ፡ አለን ፡ እኛ ፡ ኑ ፡ ወደ ፡ እኛ
ሥሙ ፡ ኢየሱስ ፡ መድኃኒ ፡ ዓለም
እንደርሱ ፡ ያለ ፡ የትም ፡ የለም
ፀንቶ ፡ የሚኖር ፡ ለዘለዓለም (፪x)
እውነት ፡ ሕይወት ፡ መንገድ ፡ እርሱ
ለነፍስ ፡ መዳን ፡ ለሥጋ ፡ ፈውሱ
ድምፁን ፡ ስሙ ፡ ተመለሱ
ወደ ፡ እርሱ ፡ ኑ ፡ ዛሬውኑ (፭x)