አለኝ ፡ ቀጠሮ (Alegn Qetero) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታምራት ፡ ሃይሌ
(Tamrat Haile)

Lyrics.jpg


(6)

ኢየሱስ ፡ ገናና ፡ ነው
(Eyesus Genana New)

ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 7:27
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ሃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

አዝ፦ አለኝ ፡ ቀጠሮ ፡ ኢየሱስ ፡ ከሚባል ፡ እንግዳ
እስኪ ፡ ልነሳ ፡ ቤቴን ፡ ላሰናዳ (፪x)

ሰዓቱ ፡ አይታወቅ ፡ መምጫው ፡ እንደ ፡ ሌባ
ኮቴው ፡ አይሰማም ፡ ሲወጣ ፡ ሲገባ
ድምፁ ፡ ሰው ፡ አይረብሽ ፡ አያውክ ፡ ጩኸቱ
በድንገት ፡ ይሆናል ፡ የኢየሱስ ፡ መምጣቱ

አዝ፦ አለኝ ፡ ቀጠሮ ፡ ኢየሱስ ፡ ከሚባል ፡ እንግዳ
እስኪ ፡ ልነሳ ፡ ቤቴን ፡ ላሰናዳ (፪x)

እንግዳ ፡ ጋብዤ ፡ ምንድነው ፡ መኝታ
ለቀን ፡ ምሳ ፡ ልስራ ፡ እራቱን ፡ ለማታ
ነቅቼ ፡ ልጠብቅ ፡ የሕይወቴን ፡ ጌታ
ወገቤን ፡ አጥብቄ ፡ ልበል ፡ ማራናታ

አዝ፦ አለኝ ፡ ቀጠሮ ፡ ኢየሱስ ፡ ከሚባል ፡ እንግዳ
እስኪ ፡ ልነሳ ፡ ቤቴን ፡ ላሰናዳ (፪x)

ላልዳኑ ፡ ልመስክር ፡ የዳኑትን ፡ ላፅና
ትእዛዝ ፡ አልጠብቅም ፡ ተግባሬ ፡ ነውና
ቅዱስ ፡ ቃሉን ፡ ላጥና ፡ በፀሎትም ፡ ልትጋ
የገሃነምን ፡ ደጅ ፡ በስሙ ፡ ልዋጋ

አዝ፦ አለኝ ፡ ቀጠሮ ፡ ኢየሱስ ፡ ከሚባል ፡ እንግዳ
እስኪ ፡ ልነሳ ፡ ቤቴን ፡ ላሰናዳ (፪x)

ሕይወት ፡ መቅኖ ፡ የለው ፡ ያልፋል ፡ እንደ ፡ ጤዛ
ልቦናዬን ፡ ላጥራ ፡ እስኪ ፡ እራሴን ፡ ልግዛ
ስለ ፡ ኀጢአቴ ፡ አምርሬ ፡ አለቅሳለሁ
ለንስሐ ፡ ፆም ፡ እቀድሳለሁ

አዝ፦ አለኝ ፡ ቀጠሮ ፡ ኢየሱስ ፡ ከሚባል ፡ እንግዳ
እስኪ ፡ ልነሳ ፡ ቤቴን ፡ ላሰናዳ (፪x)

የበደልኩትን ፡ ሰው ፡ ይቅርታ ፡ ልጠይቅ
የበደለኝም ፡ ካለ ፡ ፈጥኜ ፡ ልታረቅ
እርሾና ፡ እርም ፡ ይዜ ፡ መኖርም ፡ ይቅርብኝ
ከፍቅር ፡ በስተቀር ፡ እዳ ፡ እንዳይኖርብኝ

አዝ፦ አለኝ ፡ ቀጠሮ ፡ ኢየሱስ ፡ ከሚባል ፡ እንግዳ
እስኪ ፡ ልነሳ ፡ ቤቴን ፡ ላሰናዳ (፪x)