From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ የማይከዳ
ኑሮ ፡ ቢሆን ፡ ምድረ ፡ በዳ
የቀረበ ፡ ሲርቅ ፡ ያጀበ ፡ ሲበተን
ዞር ፡ ቀና ፡ ብዬ ፡ ሳይህ ፡ አላጣሁም ፡ አንተን
አብርሃም ፡ በእምነት ፡ ቢወጣ ፡ ከኡር (፪x) [1]
ተስፋው ፡ ቢረዝምበት ፡ ገባው ፡ ጥርጥር (፪x) [2]
የተረሳ ፡ ቢመስል ፡ ዘመኑም ፡ ያለፈ (፪x)
ተስፋውን ፡ ፈጸምክለት ፡ ቃልህ ፡ መች ፡ ታጠፈ (፪x) [3]
አዝ፦ አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ የማይከዳ
ኑሮ ፡ ቢሆን ፡ ምድረበዳ
የቀረበ ፡ ሲርቅ ፡ ያጀበ ፡ ሲበተን
ዞር ፡ ቀና ፡ ብዬ ፡ ሳይህ ፡ አላጣሁም ፡ አንተን
እንጀራ ፡ የበላ ፡ ፈውስ ፡ የተቀበለ
ፀሐይ ፡ ቆልቆል ፡ ሲል ፡ አንድ ፡ እንኳ ፡ የታለ (፪x)
የሰው ፡ አለኝታነት ፡ ዘለቄታ ፡ የለው
በሆሳእና ፡ ማግስት ፡ ስቀለው ፡ ስቀለው (፪x)
አዝ፦ አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ የማይከዳ
ኑሮ ፡ ቢሆን ፡ ምድረ ፡ በዳ
የቀረበ ፡ ሲርቅ ፡ ያጀበ ፡ ሲበተን
ዞር ፡ ቀና ፡ ብዬ ፡ ሳይህ ፡ አላጣሁም ፡ አንተን
ኑሃሚን ፡ በሞአብ ፡ ህይወት ፡ ሲመራት
የልጇ ፡ ሚስት ፡ ኦርፋ ፡ ስማ ፡ ተለየቻት (፪x) [4]
ጊዜና ፡ ሁኔታ ፡ አላምር ፡ ሲላቸው
ስመው ፡ የሚለዩ ፡ ዛሬም ፡ ብዙ ፡ ናቸው (፪x)
አዝ፦ አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ የማይከዳ
ኑሮ ፡ ቢሆን ፡ ምድረ ፡ በዳ
የቀረበ ፡ ሲርቅ ፡ ያጀበ ፡ ሲበተን
ዞር ፡ ቀና ፡ ብዬ ፡ ሳይህ ፡ አላጣሁም ፡ አንተን
ሳኦል ፡ ሰይፉን ፡ ሲስል ፡ በቤተ-መንግስቱ
ጋሻ ፡ ጃግሬዎቹም ፡ አብረው ፡ ሲዶልቱ (፪x)
ትልቁም ፡ ትንሹም ፡ ዳዊትን ፡ ሲያወግዝ
ማን ፡ ይሆን ፡ ዮናታን ፡ ምስኪኑን ፡ የሚያግዝ
ለምስኪኑ ፡ የሚያግዝ
አዝ፦ አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ የማይከዳ
ኑሮ ፡ ቢሆን ፡ ምድረ ፡ በዳ
የቀረበ ፡ ሲርቅ ፡ ያጀበ ፡ ሲበተን
ዞር ፡ ቀና ፡ ብዬ ፡ ሳይህ ፡ አላጣሁም ፡ አንተን
ተስፋዬ ፡ ተሟጦ ፡ ቀን ፡ የጐደለ ፡ ዕለት
ባለዕዳ ፡ ሲመኘኝ ፡ ለዳግም ፡ ባርነት (፪x)
ሰማይም ፡ ነደደ ፡ ማድጋዬን ፡ ሞላው
እዳዬ ፡ ተከፍሎ ፡ ተረፈኝ ፡ የምበላው (፪x)
አዝ፦ አለኝ ፡ ወዳጅ ፡ የማይከዳ
ኑሮ ፡ ቢሆን ፡ ምድረ ፡ በዳ
የቀረበ ፡ ሲርቅ ፡ ያጀበ ፡ ሲበተን
ዞር ፡ ቀና ፡ ብዬ ፡ ሳይህ ፡ አላጣሁም ፡ አንተን
|
- ↑ ዘፍጥረት ፲፪ ፡ ፩ - ፮ (Genesis 12:1 - 6)
- ↑ ዘፍጥረት ፲፯ ፡ ፲፯ (Genesis 17:17)
- ↑ ዘፍጥረት ፳፩ ፡ ፪ - ፫ (Genesis 21:2-3)
- ↑ ሩት ፩ ፡ ፲፬ (Ruth 1:14)