ምድር ፡ ሰፊ ፡ ናት (Meder Sefi Nat) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታምራት ፡ ሃይሌ
(Tamrat Haile)

Tamrat Haile 9.jpeg


(9)

እግዚአብሔር ፡ ተራራዬን ፡ አናገረው
(Egziabhier Terarayien Anagerew)

ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 6:07
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ሃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamrat Haile)

አዝ፦ ምድር ፡ ሰፊ ፡ ናት ፡ ምን ፡ ያገፋፋናል
መነካከሳችን ፡ ያጠፋፋናል (፪x)

የፍቅርን ፡ ጌታ ፡ እያመለክን
የፍቅርን ፡ ወንጌል ፡ እየሰበክን
መኖር ፡ ስንችል ፡ ተዘልለን
ጠላት ፡ በዘዴ ፡ ሥራ ፡ ሰጠን
ፍቅርን ፡ አሳዶ ፡ ጥልን ፡ አንግሶ
በዓለም ፡ መድረክ ፡ ወንድሙን ፡ ከሶ
ቢያዜም ፡ ቢጸልይ ፡ እንዳይቀር ፡ ወጉ
ማን ፡ ተባረከ ፡ እስኪ ፡ ፈልጉ

አዝ፦ ምድር ፡ ሰፊ ፡ ናት ፡ ምን ፡ ያገፋፋናል
መነካከሳችን ፡ ያጠፋፋናል (፪x)

የራሱን ፡ ሰርቶ ፡ የሌላውን ፡ ሊያፈርስ
አንዱ ፡ በሌላው ፡ ከንፈሩን ፡ ሲነክስ
ጠላት ፡ ከኋላ ፡ ድንበር ፡ ሲገፋ
አርቆ ፡ አሳቢ ፡ አስተዋይ ፡ ጠፋ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ የሞተላቸው
በጐቹ ፡ ሁሉ ፡ የእርሱ ፡ ናቸው
በማን ፡ ርስት ፡ ነው ፡ የምንጣላው
እንመለስ ፡ ፍርድ ፡ አለ ፡ ኋላ

አዝ፦ ምድር ፡ ሰፊ ፡ ናት ፡ ምን ፡ ያገፋፋናል
መነካከሳችን ፡ ያጠፋፋናል (፪x)

በአንድ ፡ ቤት ፡ ማደር ፡ ቢያቅታቸው
አብርሃምና ፡ ሎጥ ፡ ቤተሰብ ፡ ናቸው
ችለው ፡ የለም ፡ ወይ ፡ ግራ ፡ ቀኝ ፡ መሄድ
ከማን ፡ ተማርነው ፡ ወገን ፡ ማሳደድ
ለምንኖርባት ፡ ለዚህች ፡ ምድር
ተስፋዋ ፡ ማነው ፡ ያለእግዚአብሔር
ፍቅርና ፡ ብርሃን ፡ በእኛ ፡ ከጠፋ
በቃ ፡ አለቀላት ፡ የላትም ፡ ተስፋ

አዝ፦ ምድር ፡ ሰፊ ፡ ናት ፡ ምን ፡ ያገፋፋናል
መነካከሳችን ፡ ያጠፋፋናል (፪x)

ፍቅር ፡ ርቦናል ፡ ፍቅር ፡ ጠምቶናል
ነገር ፡ ክርክር ፡ አንገላቶናል
እናንት ፡ አባቶች ፡ ፍቅርን ፡ መግቡ
ከተስፋው ፡ አገር ፡ በሰላም ፡ አግቡ

አዝ፦ ምድር ፡ ሰፊ ፡ ናት ፡ ምን ፡ ያገፋፋናል
መነካከሳችን ፡ ያጠፋፋናል (፪x)