From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ላደረግህልኝ ፡ የምመልሰው
አንዳች ፡ የለኝም ፡ እጄም ፡ ባዶ ፡ ነው
እንካ ፡ ተቀበል ፡ የአፌን ፡ ምሥጋና
በእጄ ፡ ያለው ፡ ይኸው ፡ ነውና (፪x)
አንደበት ፡ የለኝ ፡ ሥምህን ፡ ልጠራ
ምላስም ፡ የለኝ ፡ ሥራህን ፡ ላወራ
ልናገርም ፡ ብል ፡ ጊዜም ፡ አይበቃ
ተመስገን ፡ ብዬ ፡ በአጭሩ ፡ ላብቃ (፪x)
አዝ፦ ላደረግህልኝ ፡ የምመልሰው
አንዳች ፡ የለኝም ፡ እጄም ፡ ባዶ ፡ ነው
እንካ ፡ ተቀበል ፡ የአፌን ፡ ምሥጋና
በእጄ ፡ ያለው ፡ ይኸው ፡ ነውና (፪x)
በፍቅር ፡ ቃልህ ፡ ልቤን ፡ ስትመታ
ነፍሴን ፡ ሥጋዬን ፡ ከእስር ፡ ስትፈታ
ምን ፡ አለኝና ፡ ምኔን ፡ ልክፈልህ
ከተቀበልኸኝ ፡ ክበር ፡ ልበልህ (፪x)
አዝ፦ ላደረግህልኝ ፡ የምመልሰው
አንዳች ፡ የለኝም ፡ እጄም ፡ ባዶ ፡ ነው
እንካ ፡ ተቀበል ፡ የአፌን ፡ ምሥጋና
በእጄ ፡ ያለው ፡ ይኸው ፡ ነውና (፪x)
ከትቢያ ፡ አንስተህ ፡ ሰው ፡ ስታደርገኝ
በነፍስ ፡ በሥጋ ፡ ስትባርከኝ
ሰማያዊ ፡ ፍቅርህ ፡ ልቤን ፡ ሲሞላ
ተመስገን ፡ እንጂ ፡ የለኝም ፡ ሌላ (፪x)
አዝ፦ ላደረግህልኝ ፡ የምመልሰው
አንዳች ፡ የለኝም ፡ እጄም ፡ ባዶ ፡ ነው
እንካ ፡ ተቀበል ፡ የአፌን ፡ ምሥጋና
በእጄ ፡ ያለው ፡ ይኸው ፡ ነውና (፪x)
|